26-48 ሙሴ – ሳሙኤል
Moses – Samuel

በታሪክ 26-48 ፈልግ፡
26. ሕፃኑ ሙሴ
ዘጸአት 1፥1-2፥10
ዮሴፍ ከሞተ በኋላ፥ የእስራኤል ሕዝብ በግብጽ ሀገር እጅግ በዙ። የእስራኤልንም ሕዝብ የሚያስጨንቅ ክፉ ንጉሥ ተነሳ። ይህም ንጉሥ ዮሴፍ ለግብጽ ያደረገውን መልካም ስራ አያውቅም ነበር። ስለዚህ ንጉሡ ከባድ ስራ እንዲሰሩ አዘዛቸው። እነርሱም እየበዙ ስለሄዱ ፈራ።
በዚህም ምክንያት ወንድ ልጅ ሲወለዱ እንዲገደል ትእዛዝ ሰጠ። አንዲት እስራኤላዊ እናት ግን ሙሴ የተባለ ሕፃን ልጅ ወለደች። ለሦሥት ወርም በቤቷ ደበቀችው።
በኋላ ግን በተንሳፋፊ ቅርጫት ውስጥ አስተኝታ በወንዝ ዳር ባለ ሣር ውስጥ አስቀመጠችው።
ብዙም ሳይቆይ የንጉሡ ልጅ አገኘችው። በጣም ስላዘነችለት ወስዳ እንደ ልጇ አድርጋ አሳደገችው።
Baby Moses 
Exodus 1:1-2:10
After Joseph died the Israelites kept growing in number. Eventually an evil king rose to power who oppressed the Israelites. He didn’t know about all the good things Joseph had done for Egypt. So he ordered them to work hard for him. Because the Israelites were becoming so many, he was afraid of them. He even ordered that when a baby boy was born, it should be killed. But one Israelite mother hid her baby called Moses for three months at home. Afterwards she laid him in a basket that could float and secretly put it between the reeds of the River Nile. But soon the daughter of the king found him. And because she felt sorry for him, she took him and raised him like her own son.

የንጉሡ ልጅ ሙሴን ስታገኝ
ሙሴ የተባለውን ሕፃን ልጅ ማን አሳደገው? 
የግብጽ ንጉሥ ልጅ አግኝታ ወስዳ እንደ ልጇ አድርጋ አሳደገችው።
27. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው 
ዘጸአት 2፥11-3፥22
ሙሴ በንጉሥ ቤት አደገ። እዚያም እያለ ጠንካራ እና የተማረ ሰው ሆነ። በኋላም የእስራኤልን ሕዝብ ሊረዳቸው ሞከረ። ንጉሡም ይህንን ሲሰማ ተቆጣው። ስለዚህ ሙሴ ወደ በረሀ ሸሸ። እዚያም ለብዙ ዓመታት ኖረ። ሚስትም አግብቶ ልጆችን ወለደ።
ከዕለታት አንድ ቀን ሙሴ በቁጥቋጦ ውስጥ እሳት አየ። ሆኖም ግን እሳቱ ቁጥቋጦውን አላቃጠለውም። እግዚአብሔር በቁጥቋጦው ውስጥ ነበር። እርሱም “እኔ የአብርሃም፥ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ ነኝ። እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ” ብሎ ተናገረው። ደግሞም እንዲህ አለው “የሕዝቤን ልቅሶ እና ጩኸት ስለሰማሁ፥ ቃል በገባሁት መሰረት እረዳቸዋለሁ” አለው።
ሙሴንም የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ሀገር ነጻ እንዲያወጣቸው አዘዘው።
God Calls Moses 
God Calls Moses
Exodus 2:11-3:22
Moses grew up in the king’s palace. He became a strong and smart man there. And in his position, he tried to help the people of Israel. But when the king heard about this, he became angry. So Moses fled to the desert and lived there for many years. He also got married there and had children.
One day, Moses saw fire inside a thorn bush. But the fire didn’t burn the bush up, because God was in it. He said to Moses, “I am the God of Abraham, Isaac and Jacob! I am your God. I will help my people as I promised, because I have noticed their tears and their cry for help!”
Therefore, God told Moses to go and free the people of Israel from Egypt.

ሙሴ በቁጥቋጦ ውስጥ እሳት ሲያይ
እግዚአብሔር ሙሴን ምን እንደያደርግ አዘዘው? 
ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ሀገር ነጻ እንዲያወጣቸው አዘዘው።
28. ሙሴ ወደ ግብጽ ተመለሰ
ዘጸአት 4-7
እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ግብጽ ሀገር ሄዶ የእስራኤልን ሕዝብ ነፃ እንዲያወጣ አዝዞት ነበር። ሙሴ ግን ስለፈራ፥ ወደ ግብጽ ለመመለስ አልፈለገም። ሆኖም እግዚአብሔር ስለተናገረው ታዝዞ ሄደ። ወንድሙ አሮንም እንደሚረዳው እግዚአብሔር ነገረው። ስለዚህ ሙሴ እና አሮን ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደው “እግዚአብሔር ‘ሕዝቤን ልቀቅ!’ ብሎሃል” ሲሉ ተናገሩት። ንጉሡ ግን እንቢ አለ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ከሁሉ የሚበልጥ ታላቅ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ይህ ተአምር በሙሴ እና በአሮን በኩል አደረገ፡ አሮን በትሩን ሲጥል፥ እባብ ሆነ። ይህች እባብም የሌሎቹ እባቦች ዋጠቻቸው። ቢሆንም ንጉሡ ሕዝቡን ለመልቀቅ አልፈልግም ነበር። እግዚአብሔር ግን “በእርግጥ ሕዝቤን አስለቅቃለሁ” አለ። ግብጻውያንንም ብዙ መከራ በመላክ አስጠነቀቃቸው።
Moses Returns to Egypt
Exodus 4-7
God had commanded Moses to go and lead the Israelites out of Egypt. But because Moses was afraid, he didn’t want to go back there. However, since God had sent him, he obeyed and went. God also told him that his brother Aaron would help him. So Moses and Aaron went to the King of Egypt and said, “God is telling you, ‘Let my people go!’” But the king refused. And so God did a miracle through Moses and Aaron to show that he is the Most High God. When Aaron threw his staff down, it became a snake. And it swallowed the snakes of all the other men. Nevertheless, the king didn’t want to let the people go. But God asserted, “I will surely set my people free!” And he warned the Egyptians by sending them many troubles.

የሙሴ በትር እባብ ስትሆን
ሙሴ ቢፈራም፥ ለምን ወደ ግብጽ ሀገር ተመለሰ?
የተመለሰው እግዚአብሔር ስላዘዘው ነው።
29. የበግ ደም
ዘጸአት 12
በመጨረሻም እግዚአብሔር ለሙሴ እና ለአሮን “ለእስራኤል ሕዝብ እያንዳንዱ ቤተሰብ በግ እንዲያርድ እና ደሙን በበሩ ላይ እንዲቀባ እዘዙ!“ አላቸው። ስጋውንም ደግሞ ጠብሰው እንዲበሉ ተናገራቸው። ሕዝቡም እግዚአብሔር እንዳላቸው አደረጉ።
በዚያን ሌሊት ከግብጻውያን ብዙዎች ሞቱ። የበግ ደም በበራቸው ላይ የቀቡ እስራኤላውያን ግን ምንም ሰው አልሞተባቸውም። ከዚህ በኋላ የግብጽ ንጉሥ እስራኤላውያንን ሀገሩን ለቀው እንዲሄዱ አስቸኮላቸው። ስለዚህ በፍጥነት ከግብጽ ወጡ። እግዚአብሔር በታላቅ ኃይሉ እስራኤላውያንን ከባርነት ነፃ አወጣቸው።
The Blood of the Lamb
Exodus 12
Finally, God said to Moses and Aaron, “Each Israelite family must slaughter a lamb and put its blood on their door frame! Tell them to follow this instruction.” He also commanded them to grill the meat and eat it. And the people did as God had told them.
That night, many, many Egyptians died. But no one died in the Israelite homes who put the blood of the lamb on their door frames. After this, the king commanded the Israelites to quickly leave his country. And so they left Egypt in a hurry. God freed them from slavery by his great power.

እስራኤላውያን የበጉን ደም በበራቸው ላይ ሲቀቡ
ከግብጻውያን ብዙ ሰዎች ሲሞቱ፥ ከእስራኤላውያን መካከል አንድም ሰው ያልሞተው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው የበግ ደም በበራቸው ስለቀቡ፥ ምንም ሰው አልሞተባቸውም።
30. የእስራኤላውያን ማምለጥ
ዘጸአት 14
እግዚአብሔር እንዳለው እስራኤላውያን ከግብጽ ሀገር ወጡ። እዚያ ያለውን በረሀ አቋርጠው በመሄደ ቀይ ባሕር ደረሱ። ከዚያም በኋላ ግብጻውያን በቁጣ ተከትለዋቸው መጡ። በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ወዴት መሸሽ እንደሚችሉ ስላላወቁ፥ በጣም ፈሩ። ስለዚህ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም በሙሴ በኩል ተአምር በማድረግ በፊታቸው ያለውን ባሕር ከፍሎ መንገድ አደረገላቸው። ሕዝቡም በባሕሩ መካከል በመሄድ ከጠላቶቻቸው አመለጡ። አሁንም ግብጻውያን ከኋላቸው ተከተሏቸው። ነገር ግን እስራኤላውያን ባሕሩን ከተሻግሩ በኋላ፥ እግዚአብሔር ውሃውን ወደ ግብጻውያን እንዲመለስ አደረገ። እነርሱም በውሃው ውስጥ ሞቱ። እስራኤላውያን ግን ስላዳናቸው እግዚአብሔርን በጣም አመሰገኑ።
The Israelites Escape
Exodus 14
Just as God had said, the Israelites left Egypt. They went through the desert and arrived at the Red Sea. But then the Egyptians came after them in anger. Since the Israelites didn’t know where to run, they were terrified and cried to God for help. God then did a miracle through Moses: he divided the sea in front of them and made a road through it. And in this way, the people were able to escape from their enemies through the sea. The Egyptians still chased after them. But when the Israelites had arrived at the other side of the sea, God made the water return and flow over the Egyptians. They died in the water. And the Israelites praised God for saving them.

ሙሴ እና ሕዝቡ በባሕር መካከል ሲሄዱ፥ እግዚአብሔር ከኋላቸው በደመና ውስጥ ሆኖ ሲጠብቃቸው
እስራኤላውያን ከግብጻውያን እንዲያመልጡ የረዳቸው ማን ነው?
የረዳቸው እግዚአብሔር ነው።
31. እግዚአብሔር ሕዝቡን በበረሀ መገባቸው
ዘጸአት 16-17
እስራኤላውያን አብዛኛውን ጊዜ መኖር በማይቻልበት በረሃ ውስጥ ጉዟቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ምንም በሌለበት በረሀ ለሕዝቡ ከሰማይ የሚበሉትን ምግብ ሰጣቸው። ያንንም ምግብ መና ብለው ጠሩት። እነርሱ በየቀኑ ከመሬት የሚሰበስቡትን መና ይበሉ ነበር።
እንድ ጊዜም በበረሀ እያሉ የሚጠጡት ውሃ አጡ። ከዚህም የተነሳ በሙሴ እና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ተናገሩ። ሕዝቡ ግን እግዚአብሔርን መታመን ነበረበት። ስለዚህ ሙሴም “ለምን በእኔ እና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ንግግር ተናገራችሁ?” አላቸው። ሆኖም ግን ሙሴ እግዚአብሔርን ውሃ እንዲሰጣቸው ለመነ። እግዚአብሔርም ሙሴን በበትሩ አንድ ዐለት እንዲመታ ተናገረው። ዐለት ማለት በጣም ትልቅ ድንጋይ ነው። ሙሴም በበትሩ ዐለቱን ሲመታው ውሃ ፈሰሰ። ውሃውም ከአንድ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ እስራኤላውያን የሚበቃ ነበር።
God Provides for His People in the Desert
Exodus 16-17
The Israelites continued their journey through the desert, where usually it’s impossible to live. But God provided them with food from heaven. They called it manna. Every day the people ate the manna which they simply collected from the ground.
One time the people didn’t have enough water to drink in the desert. And they started to talk badly against Moses and God when instead, they should have trusted in God. So Moses asked them, “Why do you insult me and God?” But he still prayed that God would give them water. And God answered him. He told him to hit a certain rock. After Moses did that, water came out of the rock and more than one million Israelites had enough to drink.

ሕዝቡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ውሃ ሲጠጡ እና ምግብ (መና) ሲሰበሰቡ
እንዴት እስራኤላውያን ምንም በሌለበት በረሀ መኖር ቻሉ?
እግዚአብሔር የሚጠጡትን ውሃ እና ከሰማይ የሚበሉትን ምግብ ስለሰጣቸው ነው።
32. ሕግ ለሙሴ ተሰጠ
ዘጸአት 19-20 + 31፥18
አንድ ቀን እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ሲና ተራራ ላይ እንዲወጣ ተናገረው። ሕዝቡ ግን ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ አልተፈቀደላቸውም ነበር። እግዚአብሔርም ሙሴን በተራራ ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ አናገረው። በዚያም ለእስራኤል ሕዝብ አሥር ትእዛዛትን በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ጽፎ እና ሌሎች ሕጎችንም ጨምሮ ሰጣቸው።
እግዚአብሔር እነዚህን ሕጎች የሰጣቸው ከእርሱ ጋር እና እርስ በእርሳቸው በሰላም እና በፍቅር እንዲኖሩ ነበር።
Moses Receives the Law
Exodus 19-20 + 31:18
One day God told Moses to go up Mount Sinai. The people, however, were not allowed to go with him. On the mountain, God spoke to Moses from within fire and wrote ten commandments on stone tablets for the people of Israel. He also gave them other laws.
The reason God gave them these laws was so that they would live in peace and love with him and with each other.

ሙሴ የእግዚአብሔርን አሥር ትእዛዛት ይዞ ከተራራው ሲወርድ
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለሕዝቡ ምን ሰጣቸው?
ለእስራኤል ሕዝብ አሥር ትእዛዛትን እና ሌሎች ሕጎችን ሰጣቸው።
33. ኢያሱ እና ካሌብ
ዘኍልቍ 13-14
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሙሴ ከነዓን የምትባለው ሀገር ምን እንደምትመስል እንዲያዩ፥ አስራ ሁለት ሰዎችን ላከ። እነርሱም ሄደው በከነዓን የሚገኙትን ፍራፍሬዎች፥ ሰዎች እና ከተሞች አዩ። ከከነዓን ሲመለሱ፥ ያዩትን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ተናገሩ። ከእነርሱ አሥሩ “እግዚአብሔር እንዳለው፥ ሀገሪቱ ድንቅ ናት። ነገር ግን በዚያ የሚኖሩት ሰዎች እጅግ በጣም ረጃጅም እና ጠንካራ ስለሆኑ፥ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሏቸው። ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ተስፋ ቆረጡ።
ኢያሱ እና ካሌብ የተባሉት ከአሥራ ሁለቱ ሰዎች ሁለቱ ግን ሕዝቡን አበረታቱ። ለሕዝቡም “የከነዓን ሰዎች ትልልቅ ቢሆኑም፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስላለ፥ እናሸንፋቸዋለን” አሉ።
እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን እርዳታ እና ተአምራት ብዙ ጊዜ ቢመለከቱም፥ በእርሱ አልታመኑም ነበር። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር “ከኢያሱ እና ከካሌብ፥ እንዲሁም ከልጆቻችሁ በስተቀር ሁላችሁም ወደ ከነዓን ሀገር አትገቡም” አላቸው። ስለዚህም ሕዝቡ ለአርባ ዓመት በበረሀ ዞሩ።
Joshua and Caleb
Numbers 13-14
Some time later Moses sent twelve men to the land of Canaan to see what it was like. They went and saw its wonderful fruit, its people and cities.
When they returned, they told the people of Israel what they had seen. Ten of them said, “The land is wonderful just as God promised. But the people who live there are huge and very strong. We cannot conquer them!” When the Israelites heard this, they despaired.
Only two of the twelve, named Joshua and Caleb, encouraged them with the words, “Yes, the people of Canaan are strong and tall but because God is with us, we can surely conquer them!”
Although the Israelites had seen God’s help and miracles so many times, they didn’t trust in him. Then God said to them, “Besides Joshua, Caleb and your children, none of you will enter the land of Canaan.” And this is why the Israelites wandered here and there in the desert for 40 years.

የተላኩት ሰዎች ለሙሴ በከነዓን ሀገር ያዩትን ሲነግሩት
አሥሩ ሰዎች ለሕዝቡ ተስፋ የሚያስቆርጥ ንግግር ሲናገሩ፥ ኢያሱ እና ካሌብ ግን ለምን ማሸነፍ እንችላለን አሉ?
እግዚአብሔር እንደሚረዳቸው ስላመኑ ነው።
34. ከመርዘኛ እባብ መዳን
ዘኍልቍ 21
እስራኤላውያን በበረሀ ሲጓዙ፥ እግዚአብሔር የሚያስፈልጋቸውን ሰጣቸው። እነርሱ ግን ሊረኩ አልቻሉም። በበረሀም ሲኖሩ ሳለ፥ በሕዝቡ መካከል በእግዚአብሔር እና በሙሴ ላይ ክፉ ንግግር በዛ። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር መርዘኛ እባቦችን ላከባቸው። ብዙ ሰዎችም በእባብ ተነድፈው ሞቱ። ሕዝቡም ይህንን ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠየቁ። ሙሴም እንደገና እግዚአብሔርን እንዲያድናቸው ለመነ። እርሱም ጸሎቱን ሰማ። ከናስ ብረት እባብ እንዲሰራ እና በእንጨት ሰቅሎ እንዲተክል ለሙሴ ነገረው። በእባብ የተነደፉት ሰዎች ያንን የናስ እባብ ሲመለከቱ፥ ወዲያውኑ ዳኑ።
Remedy for Deadly Snake Bites
Numbers 21
While the Israelites lived in the desert, time and again they were not satisfied with the things God provided for them. So one time, God sent lots of poisonous snakes to them because of all their bad talking against him and Moses. These snakes bit many Israelites so that they died. When the people saw this, they asked God for forgiveness. Again, Moses pleaded with God to save them. And God heard his prayer. He told Moses to put up a wooden pole with a snake made of metal hung on it. Everyone who was bitten and looked in faith at the metal snake was healed immediately.
You may also want to read John 3:14-15.

እግዚአብሔር እንደተናገረው ሙሴ የናስ እባብ ያለበትን እንጨት ሲተክል
በእባብ የተነደፉ ሰዎች እንዲድኑ፥ እግዚአብሔር ምን ዐይነት መዳኛ አዘጋጀላቸው?
የናሱን እባብ በመመልከት እንዲድኑ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በዮሐንስ 3፡14-15 ይነበብ!
35. ኢያሱ ሕዝቡን ወደ ከነዓን መራ
ኢያሱ 1-3 + ዘዳግም 34፥10
ሙሴም በአንድ ተራራ ላይ ሆኖ ከነዓንን ከሩቅ አየ። ከዚያም እዛው ተራራ ላይ ሞተ። ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያየ እና ያነጋገረ (በጣም ትሑት*) ሰው ነበር። በእስራኤል ከእርሱ በፊትም ሆነ፥ በኋላ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ አልነበረም።
ሙሴ ከሞተ በኋላ፥ እግዚአብሔር ኢያሱን መሪ አደረገው። የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ከነዓን ሀገር እንዲመራ ተናገረው። ከነዓንም እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው የተስፋ ቃል ሀገር ነበረች። ስለዚህ ኢያሱ እና ሕዝቡ ተነስተው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጡ። ወደ ከነዓን ለመሄድ ግን የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ነበረባቸው። ወንዙ ብዙ ውሃ ስለነበረው፥ መሻገር አስፈሪ ነበር። ስለዚህ በመጀመሪያ ካህናቱ ታቦት ተሸክመው በእግራቸው ወንዙ ውስጥ ገብተው ቆሙ። በዚህ ጊዜ ውሃው ቀጥ ብሎ ስለቆመ፥ በደረቅ መሬት የዮርዳኖስን ወንዝ በቀላሉ ተሻገሩ። ከዚህም በኋላ ከነዓን ደረሱ።
Joshua Leads the People into Canaan
Joshua 1-3 + Deuteronomy 34:10
Moses was allowed to see the land of Canaan from a mountain. But he didn’t enter it. He died there on the mountain. Moses had been a very humble man who talked with God face to face. There has never been any other prophet like him in Israel.
After Moses died, God told Joshua to lead the people of Israel into the land of Canaan. That was the land that God had promised to Abraham. Therefore, Joshua and the people went to the Jordan River. But to reach Canaan, they had to cross the river that was full of water – quite scary. First the priests, who carried the ark of the covenant, stepped into the river. God then stopped the water flow so that the entire population was able to cross the riverbed easily. It had become dry! They had finally reached Canaan.

እግዚአብሔር ውሃውን ሲያቆመው እና የእስራኤል ሕዝብ ሲሻገሩ
የዮርዳኖስን ወንዝ ማን አቆመው?
ወንዙን ያቆመው እግዚአብሔር ነው።
36. እስራኤል እና ኢያሪኮ
ኢያሱ 6
በከነዓን ሀገር የምትገኝ ኢያሪኮ የምትባል ከተማ ነበረች። በዙሪያዋ ከድንጋይ የተሰራ ጠንካራ አጥር ነበራት። ስለዚህ በቀላሉ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ ማሸነፍ አይቻልም ነበር። እግዚአብሔርም ለእስራኤላውያን ማሸነፍ እንዲችሉ፥ ማድረግ ያለባቸውን እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ከተማዋን ለስድስት ቀናት በፀጥታ በየቀኑ አንድ ጊዜ ዙሩ! በሰባተኛው ቀን ሰባት ጊዜ ዞራችሁ ስትጨርሱ፥ በከፍተኛ ድምፅ ጩኹ!” አላቸው።
ሕዝቡም እግዚአብሔር እንዳላቸው ከተማዋን ዞሩ። በመጨረሻም ቀን ሲጮሁ፥ የኢያሪኮ አጥር ተደረመሰ። በዚህ መንገድ ከተማዋን ማሸነፍ ቻሉ። ሆኖም ግን ከኢያሪኮ ሰዎች መካከል ቀይ ገመድ በቤታቸው የሰቀሉ አንድ ቤተሰብን አዳኗቸው። ምክንያቱም ከቤተሰቡ መካከል አንዲት ሴት ከዚህ በፊት እስራኤላውያንን ረድታቸው ስለነበረ ነው።
Israel and Jericho
Joshua 6
Jericho was a city in Canaan with a big, strong wall around it. So it wasn’t easy to enter and conquer. But God told Joshua what the Israelites must do so they could actually conquer it. He said, “For six days, walk silently around the city once! On the seventh day walk around it seven times. The last time: shout loudly!”
The Israelites walked around the city as God had told them. And on the final day when they shouted, the strong wall of Jericho collapsed. With the help of God, the people of Israel were able to conquer the city. But they spared the lives of the family who had hung a red rope on their house, because one woman of this family had previously helped the Israelites.

የኢያሪኮ አጥር በእግዚአብሔር ኃይል ሲደረመስ
የኢያሪኮን አጥር ማን ደረመሰው?
የደረመሰው እግዚአብሔር ነው።
37. እግዚአብሔርን ብቻ ማምለክ
ኢያሱ 24
ኢያሱ የእስራኤልን ሕዝብ* ለብዙ ዓመታት በጥሩ ሁኔታ መራቸው። ከመሞቱም በፊት የሕዝቡን መሪዎች ሁሉ* ሰበሰበ። ለእነርሱም እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ያደረገውን ስራ ሁሉ ነገራቸው። እግዚአብሔር ከግብጽ እንዳወጣቸው፥ በበረሀ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እንደሰጣቸው እና ወደ ተስፋይቱ ሀገር እንደመራቸው አስታወሳቸው። ከዚያም በኋላ ኢያሱ ፡- “እኔ እና ቤተሰቤ እግዚአብሔርን እናመልካለን። እናንተስ፥ ማንን ማምለክ ትፈልጋላችሁ? እግዚአብሔርን ወይስ ሌሎች አማልክቶችን?” ብሎ ምርጫ ሰጣቸው። ሕዝቡም ሁሉ“እግዚአብሔርን ማምለክ እንፈልጋለን” ብለው መለሱለት። ኢያሱም “እግዚአብሔርን ከመረጣችሁ፥ ለእርሱ ብቻ ታዘዙ!” አላቸው።
Serving God Only
Joshua 24
Joshua led the Israelites in a good way for many years. Before he died, he called all their leaders together. And he told them everything God had done for their ancestors. He reminded them that he had led them out of Egypt, that he had provided for them in the desert, and that he had led them into the promised land. Then Joshua said, “I and my family will worship God. What about you? Who do you want to worship? Choose! Do you want to worship God or other lords?” Then they all answered, “We want to worship God!” So Joshua said, “If you choose God, then serve him only!”

የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ሲወስኑ
ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወይስ ሌሎች አማልክትን መረጡ?
እግዚአብሔርን ብቻ ለማምለክ መረጡ።
38. የጌዴዎን መጠራት
መሳፍንት 6
እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ሊታዘዙ ቃል ገብተው ነበር። ሆኖም ግን ብዙ ጊዜ የገቡትን ቃል መጠበቅ አልቻሉም። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በሌላ ሕዝብ እንዲጨነቁ ይፈቅድ ነበር። እስራኤላውያንም ችግሩ እየከበዳቸው ሲመጣ፥ የእግዚአብሔርን እርዳታ ይጠይቁ ነበር። በጌዴዎንም ዘመን በጠላቶቻቸው ተጨንቀው ስለነበር፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ስለሰማ፥ አንድ ቀን መልአክ ለጌዴዎን ተገልጦለት፡- “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። በአንተም በኩል የእስራኤልን ሕዝብ ከሚያስጨንቋቸው ሰዎች ነፃ አወጣቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ ጥሩ ምግብ አቀረበ። መልአኩም ምግቡን ሳይበላ በበትሩ ነካው። እሳትም ከሰማይ መጥቶ ምግቡን አቃጠለው። በዚህም ጌዴዎን እግዚአብሔር በእውነት ሕዝቡን ለማዳን እንደመረጠው አወቀ።
The Calling of Gideon
Judges 6
The Israelites had promised to obey God and to live a life pleasing to him. But often they were not able to keep their promise. Therefore, God sometimes allowed other people to trouble them. In Gideon’s time it happened just like that – they were troubled by another people because they had done evil. As a result, they called out to God again.
Because God heard their prayers, one day an angel appeared to Gideon. He said, “I will be with you and through you I will free the Israelites from the people who trouble them!” After that Gideon brought good food to the angel of God. The angel didn’t eat it, but touched it with his staff. Suddenly fire came from heaven and burned it. This way Gideon knew for sure that God had really chosen him to rescue his people.

ጌዴዎን ለመልአኩ ምግብ ሲያቀርብ እና ምግቡ በእሳት ሲቃጠል
እግዚአብሔር ለጌዴዎን መልአኩን ለምን ላከ?
የእስራኤልን ሕዝብ ነፃ እንደሚያወጣቸው ሊነግረው ነው።
39. ጌዴዎን ከሦስት መቶ ሰዎች ጋር
መሳፍንት 7
ሕዝቡም እግዚአብሔር እንደተናገረው፥ በጌዴዎን መሪነት ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት ተዘጋጁ። እግዚአብሔር ግን ጌዴዎንን “የሕዝቡ ቁጥር ስለበዛ ቀንሳቸው!” አለው። ስለዚህ ጌዴዎን የፈሩ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አደረገ።
በድጋሜ እግዚአብሔር፡- “አሁንም ሰዎች በጣም ስለበዙ፥ መቀነስ አለባቸው። ስለዚህ ውሃ እንዲጠጡ ወደ ወንዝ አምጣቸው እና ተንበርክከው የሚጠጡትን ወደ ቤታቸው መልሳቸው!” አለው። ጌዴዎንም እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ። ከዚህ በኋላ የቀሩት ሦስት መቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ። ጠላቶቻቸውን ለመወጋት ይዟቸው ሄደ። እግዚአብሔርም ስለተዋጋላቸው፥ ብዙ ሺህ የሚሆኑ ጠላቶቻቸውን አሸነፉ። እግዚአብሔር ወደ ውጊያው ጥቂት ሰዎችን ብቻ የላከው፥ ድሉ ከእርሱ እንደመጣ እንዲያውቁ ነው።
Gideon with 300 Men
Judges 7
The people, under the leadership of Gideon, got ready to fight their oppressors as God had ordered. But then God told Gideon, “These are too many people, reduce their number!” Therefore, Gideon sent all the men who were afraid home.
Afterwards God again said to him, “There are still too many. So, take them to the river to drink! Send home those people who kneel down to drink.” Gideon followed God’s instruction and finally the men who stayed with him were only 300. Together with them Gideon went to fight the enemies. And because God helped them, they conquered their enemies even though they were many thousands. God sent only a small number of men to fight, in order to show that it was him who gave them victory.

የሰውን ቁጥር ለመቀነስ ጌዴዎን ሰዎቹ ውሃ እንዴት እንደሚጠጡ ሲመለከት
ለምን እግዚአብሔር ከጌዴዎን ጋር ሦስት መቶ ሰዎች ብቻ ለጦርነት እንዲሄዱ አደረገ?
ማሸነፍ የቻሉት በእነርሱ ኃይል ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ኃይል እንደሆነ እንዲያውቁ ነው።
40. ሳምሶን አንበሳ ገደለ
መሳፍንት 13 +14
እንደገና በሌላ ዘመን እስራኤላውያን በጣም ስለተጨነቁ፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰማ። በዚህ ጊዜ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባል እና ሚስት ልዩ ልጅ ሰጣቸው። እግዚአብሔርም ልጁ ከመወለዱ በፊት “ልጁ የእኔ መሆኑ እንዲታወቅ፥ ፀጉሩን በፍጹም አትቁረጡ!” አላቸው። እነርሱም እግዚአብሔር እንዳላቸው ፀጉሩን አልቆረጡም። ልጃቸውም እጅግ በጣም ጠንካራ ሰው ሆነ። ስሙም ሳምሶን ይባል ነበር። አንድ ጊዜ የመጣበትን አንበሳ በባዶ እጁ እግዚአብሔር በሰጠው ኃይል ገደለ።
Samson Kills a Lion
Judges 13+14
Decades later, when the Israelites were in serious trouble once more, they called to God for help again. And he heard their prayers. This time, he gave a special child to a couple that was not able to have children. Before he was born God told them, “Never cut the child’s hair, because that is the sign that he belongs to me!” They obeyed God and their child became an incredibly strong man. His name was Samson. One time, when he was attacked by a lion, he killed it with his bare hands by the power God had given him.

ሳምሶን የመጣበትን አንበሳ በእግዚአብሔር ኃይል በባዶ እጁ ሲገድል
እስራኤላውያን ከባድ ችግር ውስጥ በገቡ ጊዜ፥ ምን አደረጉ?
እንዲያድናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
41. የሳምሶን ስሕተት
መሳፍንት 16
ሳምሶን ከእስራኤል ጠላቶች የነበረችውን ደሊላ የምትባል ሴት ወደደ። እርሷም ኃይለኛ ሊሆን የቻለበትን ምስጢር ጠየቀችው። እርሱ ግን ሊነግራት አልፈለገም ነበር። ብዙ ጊዜ ስለጠየቀችው ግን፥ በመጨረሻ ሳምሶን “ፀጉሬ ከተቆረጠ፥ እንደ ማንኛውም ሰው ኃይል የሌለኝ እሆናለሁ” በማለት ምስጢሩን ነገራት። ደሊላም የሳምሶንን የኃይል ምስጢር ለጠላቶቹ ነገረቻቸው። እነርሱም እንቅልፍ ተኝቶ እያለ መጥተው ፀጉሩን ቆረጡት። ከዚህ የተነሳ ሳምሶን ደካማ ስለሆነ፥ በቀላሉ ይዘው ወደ እስር ቤት አስገቡት።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፀጉሩ እንደገና ማደግ ስለጀመረ፥ ኃይሉ ተመለሰለት። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለመርዳት ተጠቀመበት። በአንድ ግብዣ ላይ ብዙ ጠላቶቹ የሞሉበትን የትልቅ ቤት ምሶሶ ገፍቶ ቤቱ በላያቸው እንዲደረመስ አደረገ። ሳምሶንም ከብዙ ጠላቶቹ ጋር አንድ ላይ ሞተ።
ሳምሶን እስራኤልን ለመርዳት ከእግዚአብሔር ኃይል አገኘ።
Samson’s Mistake
Judges 16
Samson was in love with a woman who belonged to Israel’s oppressors. Her name was Delilah. She asked him what the secret of his power was. But he didn’t want to tell her. Yet because she didn’t stop nagging, Samson finally told her his secret, “If my hair is cut, I will be powerless like every other person.“ Delilah then revealled the secret of Samson’s power to his enemies. Soon afterwards, they came and cut his hair while he was asleep. In this way, he became weak. As a result, it was easy for them to put him in prison.
But over time Samson’s hair grew back and therefore his power also returned. God used him to help Israel in their misery. During a celebration, Samson pushed against the pillars of a big house which was full of people and caused it to collapse. This way he died together with many of his enemies.
Samson had received power from God in order to help Israel against their oppressors.

ጠላቶች የሳምሶንን ፀጉር ሲቆርጡ
42. ኑኃሚን እና ሩት
ሩት 1
ኑኃሚን የምትባል ሴት ሀገራቸው ራብ በሆነ ጊዜ ከባሏ እና ከሁለት ወንድ ልጆቿ ጋር ወደ ሌላ ሀገር ሄደች። በዚያም እየኖረች ሳለ፥ ባሏ እና ልጆቿ ሞቱባት። ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር የሌለ መስሏት ነበር። አንድ ቀን ኑኃሚን የልጆቿ ሚስቶች የነበሩትን “ከዚህ በኋላ እዚህ አልቀመጥም። ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ። እናንተም ወደ ቤተሰቦቻችሁ ተመለሱ!” አለቻቸው። አንደኛዋ በሀገሯ ለመቅረት ስትስማማ፥ ሩት ግን አብራት ለመሄድ ወሰነች። እርሷም ኑኃሚንን “ብቻሽን በፍጹም አልተውሽም። አብሬሽ እሄዳለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሆናል፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል” አለቻት። ስለዚህ ኑኃሚን እና ሩት ወደ እስራኤል ሀገር አብረው ሄዱ። እዚያም መኖር ጀመሩ።
Naomi and Ruth
Ruth 1
Due to a famine, a woman called Naomi went to a foreign country with her husband and two sons. While she was living there, her husband and her two sons died. And so she thought God was not with her. One day, Naomi said to the women who had been the wives of her sons, “I will not stay here any longer. I’ll go back to my country. You should return to your families here also!” One of them agreed, and stayed in her own land. But Ruth decided to go with Naomi. She said to her, “I will certainly not leave you alone! I’ll go with you. Your people will be my people and your God will be my God!” And so Naomi and Ruth went to the land of Israel together and started to live there.

ሩት ኑኃሚንን “ከአንቺ ጋር እሄዳለሁ” ስትላት
ኑኃሚን እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር የሌለ የመሰላት ለምንድን ነው?
ሁለቱ ልጆቿ እና ባሏ ስለሞቱባት፥ እንዲሁም ኑሮም አስቸጋሪ ስለሆነባት ነው።
43. ሩት እህል ሰበሰበች
ሩት 2
ሩት በእስራኤል ሀገር ምንም የሌላት እንግዳ ነበረች። ከኑኃሚን በስተቀር የምታውቀው ሰው አልነበራትም። አማቷንም በጣም ትረዳት እና ምክሯንም ትሰማ ነበር። አንድ ቀን እህል በሚሰበስብበት ወቅት፥ በአንድ እርሻ የተረፈ እህል ቀኑን ሙሉ ስትሰበስብ ዋለች። የእርሻው ባለቤት ቦዔዝ የተባለ መልካም እና ሀብታም ሰው ነበር። ስለ ሩትም መልካምነት ሰምቶ ነበር። ስለዚህ በእርሻው የተረፈ እህል እንድትሰበሰብ ፈቀደላት። በተጨማሪም ለሰራተኞቹ መልካም እንዲሆኑላት እና ብዙ እህል እንዲያስቀሩላት ነገራቸው። በዚህ ምክንያት ሩት በቂ እህል መሰብሰብ ቻለች።
Ruth Collects Grain
Ruth 2
Ruth was a foreigner in Israel who didn’t possess anything. And apart from Naomi she didn’t know anyone. She helped her mother-in-law a lot and followed her advice. Once, during the grain harvest, she worked the whole day collecting what remained from the harvest in a certain field. The owner of the field was called Boaz. He was a good and wealthy man who had already heard about Ruth’s kindness. Therefore, he allowed her to collect the leftover grain. He also told his workers to be kind to her and to leave behind some grain on purpose. And so Ruth was able to collect enough.

ሩት በእርሻ የተረፈውን እህል ስትሰበስብ
ሩት የሌላ ሀገር ሰው ብትሆንም፥ ቦዔዝ ረድቷታል?
አዎን፥ ረድቷታል።
44. ሩት ወደ ቦዔዝ ሄደች
ሩት 3
ኑኃሚን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሩትን ቦዔዝ መልካም ሰው ስለሆነ እንድታገባው መከረቻት። ሩትም በኑኃሚን ምክር ተስማማች። ስለዚህ ቆንጆ ልብስ ለብሳ ቦዔዝ ወዳለበት ቦታ ሄደች። እርሱንም ለማግባት ፍላጎት እንዳላት ገለፀችለት።
ቦዔዝም በመልካምነት ለሩት “ወደ ሌላ ሰው አልሄድሽም። ለቤተሰባችንም ታማኝ ስለሆንሽ፥ እግዚአብሔር ይባርክሽ! ስለ ጋብቻችን ጉዳይ ግን ከአንድ ዘመዳችን ጋር መወያየት አለብኝ። ከዚያም በኋላ መልሱን እነግርሻለሁ። አሁን ግን እህል ይዘሽ ወደ አማትሽ ወደ ኑኃሚን ሂጂ!” አላት። ከዚያም ብዙ እህል ሰጣት። ሩትም እህሉን ተሸክማ ወደ ቤት ሄዳ ለኑኃሚን ሰጠቻት።
Ruth Visits Boaz
Ruth 3
Some time later, Naomi pointed out to Ruth that Boaz would be a good man to marry. Ruth agreed with Naomi’s recommendation. So she dressed up and went to the place where Boaz was. She made clear to him that she was willing to marry him.
Boaz then kindly said to her, “You didn’t go to other men. May God bless you for being faithful to our family. First, I have to discuss our marriage matter with one of my relatives. After that I will tell you the answer. But for now, go home and take along some grain for your mother-in-law.” Then he gave her a lot of grain. Ruth carried it home and gave it to Naomi.

ሩት ወደ ቦዔዝ ልታገባው መፈለጓን ለመግለጽ ስትሄድ
ሩት እና ቦዔዝ ታማኞች ነበሩ ወይስ አልነበሩም?
ሩት እና ቦዔዝ ታማኞች ነበሩ።
45. ቦዔዝ እና ሩት ተጋቡ
ሩት 4
ቦዔዝ ከዘመዱ እና ከሽማግሌዎች ጋር ሩትን ለማግባት ስላሰበው ጉዳይ ተነጋገረ። ሁሉም ከተስማሙ በኋላ፥ ቦዔዝ እና ሩት ተጋቡ። ኢዮቤድ የሚባል ወንድ ልጅም ወለዱ። ኑኃሚንም እንደ ራስዋ ልጅ አድርጋ አሳደገችው። ኑኃሚን እና ቤተሰቧ እንደገና ጥሩ ኑሮ መኖር ጀመሩ። በብዙ መከራ ውስጥ ቢያልፉም፥ እግዚአብሔር ከዚህ ቤተሰብ ጋር ነበር። እርሱም በጣም ባረካቸው።
ኢዮቤድም በኋላ የንጉሥ ዳዊት አያት ሆነ።
Boaz and Ruth Get Married
Ruth 4
Boaz talked with his relative and with the town elders about his plan to marry Ruth. After they all agreed, Boaz and Ruth got married.
Some time later, they had a son called Obed. Naomi raised him as her own child. Finally, Naomi and her family began to live a good life again. Even when they passed through much suffering, God was with this family. He blessed them greatly.
Eventually Obed became the grandfather of King David.

የቦዔዝ ዘመድ እና ሽማግሌዎች በእነ ቦዔዝ ጋብቻ ጉዳይ ሲወስኑ
እግዚአብሔር ኑኃሚንን እና ሩትን እንዴት ረዳቸው?
እግዚአብሔር የረዳቸው ለሩት ባል እና ልጅ በመስጠት ነው።
46. እግዚአብሔር ለሐና ሳሙኤልን ሰጣት
1ኛ ሳሙኤል 1-2
ሐና ለብዙ ዓመታት ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። በዚህ ምክንያት በጣም አዝና “እግዚአብሔር ሆይ፥ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ፥ መልሼ ላንተ አገልጋይ እንዲሆን እሰጥሀለሁ። የእኔ ሳይሆን፥ የአንተ ልጅ ይሆናል” ብላ አልቅሳ ጸለየች። ስትጸልይ ያያት ካህንም “እግዚአብሔር የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት። ስለዚህም ሐና ተፅናንታ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ከአንድ ዓመት በኋላም እግዚአብሔር ለሐና ወንድ ልጅ ሰጣት። ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ሳሙኤል ትንሽ ካደገ በኋላ፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወስዳ ሰጠችው። ይህንን በማድረግ ሐና ለእግዚአብሔር የገባችውን ቃል ፈጸመች። ሳሙኤልም እዚያው አደገ። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ዔሊ የተባለውን ካህን ይረዳው ነበር።
God Gives Hannah a Child: Samuel
1 Samuel 1-2
For many years Hannah was not able to have children.And so she was very sad. She cried and prayed, “God, if you give me a son, I will give him back to you to be your servant. He will be yours, not mine!” The priest who saw her praying said to her, “May God give you what you have asked for” So Hannah went home comforted.
About a year later, God gave Hannah a son. She called him Samuel. And when Samuel was big enough, she took him to the house of God. By doing this she kept her promise. And so Samuel grew up helping Eli the priest in the house of God.

ሐና ተጨንቃ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ስትጸለይ
ሐና ለእግዚአብሔር የገባችውን ቃል ፈጽማለችን?
አዎን፥ ፈጽማለች።
47. እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው
1ኛ ሳሙኤል 3-4
አንድ ሌሊት ሳሙኤል ተኝቶ ሳለ“ሳሙኤል፥ ሳሙኤል!” የሚል ድምፅ ሰማ። ዔሊ የጠራው ስለመሰለው፥ ወደ እርሱ ሄዶ “ጠራኸኝ?” ሲል ጠየቀው። እርሱ ግን “አይ፥ አልጠራሁህም። እንደገና ተኛ!” ብሎ ተናገረው። ሳሙኤልም ለሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ ይህንን ድምፅ እየሰማ ወደ ዔሊ ሄደ። በመጨረሻም ዔሊ እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደጠራው ተረዳ። እርሱንም “ከዚህ በኋላ ድምፅ ስትሰማ፡ ‘እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁ እና እባክህ ተናገር!’ በል” አለው። ሳሙኤልም ዔሊ እንደተናገረው አደረገ። ከዚያም እግዚአብሔር ለብዙ ዓመታት ያልታዘዙትን የዔሊ ቤተሰብን እንደሚቀጣ ተናገረው።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እግዚአብሔርን ያላከበሩት ካህኑ ዔሊ እና ልጆቹ ሞቱ። ሳሙኤል ግን ለእስራኤል ሕዝብ ደህና የሚያስብ እና እውነተኛ ነቢይ ሆነላቸው።
God Calls Samuel
1 Samuel 3-4
One night, when Samuel was sleeping, he heard a voice calling, “Samuel, Samuel!” He thought that Eli had called him, so he went to him and asked, “Did you just call me?” But Eli said, “No, I didn’t call you. Go back to bed.” Samuel heard the voice three times and went to Eli each time. Finally, Eli understood that it was God who was calling Samuel. So he advised him, “If you hear the voice again, say: ‘Speak, my Lord! Your servant is listening.’”
And Samuel did what Eli had advised him. Then God told Samuel that he would punish Eli’s family who for many years had disobeyed God.
After some time, the priest Eli and his sons who had not honoured God, died. But Samuel served as a trustworthy prophet who cared well for the people of Israel.

እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሲጠራው፥ እርሱ ግን ወደ ዔሊ ሲሄድ
እግዚአብሔር ለትንሽ ልጅ ሊናገር ይችላልን?
አዎን፥ ሊናገር ይችላል!
ካህኑ ዔሊ የሞተው እግዚአብሔር ስላላከበረ ወይስ በሳሙኤል ንግግር ነው?
የሞተው ክፉ ሰው ስለነበር ነው።
48. ሳሙኤል ለእስራኤል ጸለየ
1ኛ ሳሙኤል 7
እስራኤላውያን ለብዙ ዓመታት በጠላቶቻቸው ተጨነቁ። ከዚህ የተነሳ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። ሳሙኤልም ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዲታዘዙ መከራቸው። ሕዝቡም መጥፎ ስራቸውን ትተው ለመታዘዝ ወሰኑ። ተሰብስበውም ሳሉ፥ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። የእስራኤል ጠላቶች መሰብሰባቸውን ሰምተው በክፋት ተነስተው ሊዋጓቸው መጡ። እግዚአብሔር ግን እስራኤላውያንን ረድቶ ጠላቶቻቸውን በኃይለኛ ነጎድጓድ አባረራቸው።
Samuel Prays for Israel
1 Samuel 7
The Israelites were oppressed by their enemies for many years. So they cried out to God. And Samuel advised the people to obey God. As a result, they decided to stop their evil deeds and obey him. When they were gathered, Samuel prayed for them to God. Israel’s enemies heard about their gathering and with evil intention got ready to attack them. But God helped the Israelites. Their enemies fled, because he scared them by unusual powerful thunder.

ሕዝቡ መጥፎ ስራቸውን ሲተው እና ሳሙኤልም ሲጸልይላቸው
ከሳሙኤል ጸሎት በፊት ሕዝቡ ምን ለመተው ወሰኑ?
መጥፎ ስራቸውን ለመተው ወሰኑ።
እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ የሚወድ ከሆነ፥ የእስራኤልን ጠላቶች ለምን አስደንግጦ አባረረ?
የእስራኤልን ሕዝብ በክፋት ለመውጋት መጥተውባቸው ስለነበር ነው።

በታሪክ 26-48 ፈልግ፡
