49-77 ነገሥታት እና ነቢያት
Kings and Prophets

ታሪኮችን ለመክፈት ከዚህ በታች የምትፈልጉትን ተጫኑ
49. ንጉሥ ሳኦል
1ኛ ሳሙኤል 8-10
እስከ ሳሙኤል ዘመን ድረስ እስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። ይመሩ የነበረው በመሪዎች እና በዳኞች ነበር። አንድ ቀን ሕዝቡ ሳሙኤልን “እንደሌሎች ሀገሮች ንጉሥ እንዲነግሠልን እንፈልጋለን” አሉት። እግዚአብሔር እና ሳሙኤል ግን በዚህ ልመናቸው አልተደሰቱም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ንጉሣቸው መሆን ይፈልግ ስለነበር ነው። ከዚህም የተነሳ ሳሙኤል “የሚነግሠው ንጉሥ በኃይል ይጨቁናችኃል” ብሎ አስጠነቀቃቸው።
እስራኤላውያን ግን አጥብቀው ስለፈለጉ፥ እግዚአብሔር ሳኦል የተባለውን ንጉሥ አነገሠላቸው። ሳሙኤልም ሳኦልን ዘይት ቀብቶ ባረከው። ሕዝቡንም “ሳኦል ንጉሣችሁ ነው። ትእዛዙን አክብሩ! አሁንም እግዚአብሔርን መታዘዝ ከሁሉም በላይ ያስፈልጋችኋል” አላቸው።
King Saul 
1 Samuel 8-10
Until Samuel’s time the people of Israel didn’t have a king. Instead, they had leaders and judges. One day, however, the people said to Samuel, “We want to have a king, just like other nations.” But God and Samuel were not pleased with this request. God wanted to be their only king. So Samuel warned them, “A king will harshly demand many things from you.”
But since the Israelites insisted, God made a man called Saul their king. Samuel anointed him with oil and blessed him. He said to the people, “Saul is your king. Obey his orders! And above all keep obeying God’s commands!”

ሳሙኤል ሳኦልን ዘይት ቀብቶ ሲባረክ
የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉሥ ማን ነበር? 
የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉሥ ሳኦል ነበር።
50. የሳኦል አለመታዘዝ 
1ኛ ሳሙኤል 15
ሳኦል ለተወሰነ ጊዜ ስኬታማ ንጉሥ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔርን አልታዘዝም ነበር። አንድ ቀን ሳኦል ትልቅ ጦርነት ካደረገ በኋላ፥ ሳሙኤል ወደ እርሱ መጣ። ለሳኦልም እግዚአብሔርን በፍጹም እንዳልታዘዘ ነገረው። ደግሞም “እግዚአብሔር ከስጦታ ይልቅ መታዘዝን ይወዳል” አለው። ሳሙኤልም ሳኦልን ተለይቶ ሊሄድ በፈለገ ጊዜ፥ ሳኦል ሊያስቆመው ሞከረ። ልብሱንም ይዞት ስለነበር፥ ጫፋ ተቀደደ። ወዲያውኑ ሳሙኤል “እንዲሁም ይህ ልብስ እንደተቀደደ፥ ዛሬ የእስራኤል መንግሥት ከአንተ ተቀደደ። ለሌላ ሰውም እንዲሰጥ ተወስኗል” አለው።
ይህ ሁሉ የሆነው ሳኦል እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ነበር።
Saul’s Disobedience 
1 Samuel 15
Saul was a successful king for a long time. But he did not obey God. And so one day after a big battle, Samuel came to him. He spoke with him about his unacceptable disobedience. He said to him, “God wants obedience much more than gifts!” When Samuel was about to leave, Saul tried to stop him. He grabbed Samuel by his clothes and a piece tore off. Samuel immediately responded, “Just as this piece of cloth tore off, the Kingdom of Israel is torn away from you today. God has firmly decided to give it to someone else.”
All this happened because Saul didn’t obey God.

ንጉሥ ሳኦል ሳሙኤልን ለማስቆም ሲሞክር እና ልብሱ ሲቀደድ
ሳኦል ለምን ንጉሥነቱ ተወሰደበት? 
ሳኦል እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ነው።
51. ዳዊት ተመረጠ
1ኛ ሳሙኤል 15-16
ዳዊት ወጣት በነበረበት ጊዜ ጎበዝ እረኛ ነበር። ከወንድሞቹ ሁሉ ታናሽ ቢሆንም፥ የአባቱን በጎች በታማኝነት ይጠብቅ ነበር። ጥሩ ባህሪም ነበረው። ስለዚህ እግዚአብሔር ዳዊት በሳኦል ቦታ የእስራኤል ቀጣይ ንጉሥ እንዲሆን መረጠው። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን እንዲቀባ ላከው። ነቢዩም ታዝዞ ወደ እነ ዳዊት ቤት ሄደ። ዳዊት ግን በጎች ይጠብቅ ስለነበር፥ ለአባቱ እንዲያስጠራው ነገረው።
ዳዊትም እንደመጣ ሳሙኤል በዘይት ቀብቶ ለንጉሥነት እንደተመረጠ ነገረው።ያን ጊዜ እግዚአብሔር ለዳዊት ኃይልን ሰጠው።
God Chooses David
1 Samuel 15-16
When David was young, he was a good shepherd. He watched over his father’s sheep faithfully, even though he was the youngest of all his brothers. He had good character. Therefore, God chose him to become the next king over Israel. And so God sent Samuel the prophet to anoint David. Samuel obediently went to the place where David lived. But since David was watching over the sheep, Samuel told his father to have him come home.
When David arrived, the prophet anointed him with oil and explained that God had chosen him to be the next king. At that time God gave his power to David.

ዳዊት መንጋውን በታማኝነት ሲጠብቅ
የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን የተመረጠው ሰው ማን ነው?
የተመረጠው ሰው ዳዊት ነው።
ዳዊት ምን ዐይነት ባህሪ ነበረው?
ዳዊት ጥሩ ባህሪ ነበረው።
52. ዳዊት እና ጎልያድ
1ኛ ሳሙኤል 17
አንድ ጊዜ እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ጋር ሊዋጉ በጦር ሜዳ ተሰብስበው ነበር። የዳዊት ወንድሞችም ወታደሮች ስለሆኑ፥ ውጊያ ሄደው ነበር። አባታቸውም ዳዊትን ለወንድሞቹ ምግብ እንዲወስድላቸው ላከው። ዳዊት ወደ እነርሱ በደረሰ ጊዜ፥ ጎልያድ የተባለ ሰው በሕዝቡ ላይ እየጮኸ ሲያስፈራራቸው ሰማ። እርሱም እጅግ ትልቅ እና ጠንካራ የእስራኤል ጠላት ነበር። ለብዙ ቀናትም በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ይፎክር ነበር።
ዳዊት ግን ወጣት ቢሆንም ሳይፈራ በእግዚአብሔር ኃይል ጎልያድን ሊዋጋ ሄደ። በወንጭፍ ድንጋይ አድርጎ በመወርወር ጎልያድን መቶ ገደለው። ከዚህ የተነሳ ጠላቶቻቸው ሁሉ ሸሹ። የእስራኤልም ወታደሮች አሸነፉአቸው።
David and Goliath
1 Samuel 17
On one occasion, the Israelites had gathered at the battle-field to fight off their enemies. David’s brothers were also soldiers and had gone there. So their father sent David to take them food. When he arrived there, he heard a man called Goliath shout and frighten the people. Goliath was an extremely tall and strong enemy. He had been making fun of God’s people for many days.
Even though David was still young, he was not afraid of Goliath. He went to fight him with the help of God. He put a stone in his sling, hurled it at Goliath and killed him. Then all the enemies ran away and Israel’s soldiers won the victory.

ዳዊት ትልቁን ጎልያድ በእግዚአብሔር ኃይል ሲያሸንፍ
ዳዊትን እና እስራኤልን የረዳቸው ማን ነው?
የረዳቸው እግዚአብሔር ነው።
53. ዳዊት እና ንጉሥ ሳኦል
1ኛ ሳሙኤል 26
ዳዊት ስኬታማ እና ጀግና ሰው ስለነበር፥ የእስራኤል ሕዝብ ከንጉሥ ሳኦል ይልቅ አከበሩት። ከዚህ የተነሳ ሳኦል “ዳዊት በእኔ ፈንታ ንጉሥ ሊሆን ነው?” ብሎ ስላሰበ ፈራ። ስለዚህ ዳዊትን ብዙ ጊዜ ለመጉዳት እና ለመግደል ይሞክር ነበር። ቢሆንም እግዚአብሔር ዳዊትን ይጠብቀው ስለነበር፥ አልተሳካለትም። ዳዊት ግን በተደጋጋሚ ሳኦልን የመግደል አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። ሆኖም እግዚአብሔር የሾመውን ሰው አልጎዳም በማለት ክፉ ነገር አላደረገበትም። ይልቁንም ለሳኦል ብዙ መልካም ነገሮችን አደረገ።
David and King Saul
1 Samuel 26
Since David was a successful and brave man, the people of Israel honoured him more than King Saul. As a result, Saul started to fear that David would become king instead of him. Consequently, many times he tried to harm and even kill David. But he was not able to do so, because God protected David.
More than once, David had the chance to kill Saul. But he didn’t do the king any evil, because he didn’t want to harm the man God had appointed. On the contrary, he did many good things to Saul.

ዳዊት ንጉሥ ሳኦልን አልጎዳም ብሎ ሲሄድ
ዳዊት ሳኦልን ያልጎዳው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር የሾመውን ሰው መጉዳት ስላልፈለገ ነው።
54. ዳዊት ንጉሥ ሆነ
2ኛ ሳሙኤል 5 + 1ኛ ዜና 22
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ሳኦል እና ሁለት ልጆቹ በጦርነት ሞቱ። ከዚያም ዳዊት ይሁዳ በሚባል የሀገሪቱ ክፍል፥ ቀጥሎም በእስራኤል ሀገር ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆነ።
ዳዊት ስህተት ቢያደርግም፥ እግዚአብሔርን የሚወድ እና የሚያከብር ንጉሥ ነበር።ለራሱም ክብር ብዙ የሚጨነቅ ሰው አልነበረም። ለእስራኤል ሕዝብም ጥሩ የሚያስብ ንጉሥ ነበር። በተጨማሪም ዳዊት ለእግዚአብሔር ብዙ መዝሙሮችን ይጽፍ፥ በገናም ይጫወት ነበር።
እርሱንም ከመውደዱ የተነሳ ቤት ሊሰራለት አሰበ። እግዚአብሔር ግን ዳዊት ብዙ ጦርነቶች ስላደረገ አልፈቀደለትም። ሆኖም “ልጅህ ሰሎሞን ቤት ይሰራልኛል” አለው።
David Becomes King
2 Samuel 5 + 1 Chronicles 22
Some years later, Saul and two of his sons died in battle. After that, David first became king over one part of the country called Judah. Later he became king over all of Israel.
Although he made mistakes, he was a king who loved and honoured God. He was not very concerned about his own honour. David was a good king for the people of Israel. He also played the harp and wrote many songs for God.
Out of his love for God, David wanted to build a house for him. But God didn’t allow him, because he had fought so many wars. Instead he assured him, “Your son Solomon will build a house for me.”

እግዚአብሔር እንደወሰነው ዳዊት ንጉሥ ሆኖ ሲሾም
ዳዊት ምን ዐይነት ንጉሥ ነበር?
እግዚአብሔርን የሚወድ፥ ለራሱ ክብር ብዙም የማይጨነቅ እና ለእስራኤልም ሕዝብ ጥሩ የሚያስብ ንጉሥ ነበር።
55. ዳዊት እና ቤርሳቤህ
2ኛ ሳሙኤል 11-12
አንድ ቀን ንጉሥ ዳዊት በቤቱ ከፍታ ቦታ ላይ ሆኖ ቤርሳቤህ የምትባል ሴት ስትታጠብ አይቶ ተሳሳተ። እርሷ ግን ባል ነበራት። ቢሆንም ዳዊት ባሏን አስገደለ። ቤርሳቤህንም ሚስቱ እንድትሆን ወሰዳት።
ዳዊትም ያደረገው ነገር በጣም የተሳሳተ እንደነበር ካወቀ በኋላ ወዲያውኑ* እግዚአብሔርን ይቅርታ ለመነ። እግዚአብሔር ጻድቅ እና መሐሪ ስለሆነ፥ ዳዊትን በጣም ቢቀጣውም ምሕረት አደረገለት። ስለዚህ ዳዊት ብዙ ዓመታት ኖረ።
David & Bathsheba
2 Samuel 11-12
One day King David was on the flat roof of his house. From there he saw a beautiful woman in the neighbourhood washing herself. David then did something wrong. The woman’s name was Bathsheba, and she was married. David ignored this, he caused her husband to die and took her to be his wife.
As soon as David realised that what he did was very wrong, he immediately asked God for forgiveness. Since God is both righteous and merciful, he had mercy on David, although he seriously punished him. Due to God’s mercy, David still lived for many years afterwards.

ዳዊት የጎረቤቱን ሚስት ሲያይ
እግዚአብሔር ለዳዊት ምሕረት ያደረገው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ እና ዳዊትም ከልቡ ይቅርታ ስለጠየቀው ነው።
56. ንጉሥ ሰሎሞን
1ኛ ነገሥት 1-8 (2ኛ ዜና 1)
ንጉሥ ዳዊት ከሞተ በኋላ፥ ልጁ ሰሎሞን በእርሱ ቦታ ነገሠ። አንድ ሌሊት እግዚአብሔር ሰሎሞንን በሕልሙ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ሰሎሞንም “ሕዝብህን በመልካም ሁኔታ መምራት እንድችል ጥበብ እና ማስተዋል ስጠኝ” ብሎ ለመነው። ሰሎሞን ለራሱ ሀብት፥ ክብር እና ሰላማዊ ኑሮ ስላልጠየቀ፥ እግዚአብሔር ከሌሎች ሰዎች ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ጥበብን ሰጠው። እንዲሁም ያልጠየቀውን ሀብት እና ክብርም ጨመረለት። ሰሎሞንም የተሰጠውን ጥበብ የእስራኤልን ሕዝብ በደህና መንገድ ለማስተዳደር እና ለመፍረድ ተጠቀመበት።
በተጨማሪም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ ሰራ። ይህም ቤት ትልቅ እና በጣም የሚያምር ሆነ። ለብዙ ዘመን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔርን ለማምለክ ወደዚያ ቤት ይሄዱ ነበር።
King Solomon
1 Kings 1-8
After King David died, his son Solomon became king in his place. One night God asked Solomon in a dream, “What do you want me to give you?“ Solomon’s answer was, “Please give me understanding and wisdom so that I am able to lead your people in a way that is good for them.“ And because Solomon didn’t ask for wealth, honour or a long life for himself. God gave him much more wisdom than to any other person. He even gave him wealth and honour in addition. Solomon used the wisdom he received from God to be a good leader and judge for the people of Israel.
Furthermore, Solomon built the first temple for God. It became really big and beautiful. For a long time, all the people of Israel went there to worship God.

ንጉሥ ሰሎሞን የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ ሠርቶ ሲጸልይ
ሰሎሞን ለራሱ ብዙ ነገር ስላልፈለገ እግዚአብሔር ምን ሰጠው?
እግዚአብሔር ታላቅ ጥበብ፥ ሀብት እና ክብርን ሰጠው።
57. ቁራዎች ምግብ ለኤልያስ አመጡ
1ኛ ነገሥት 17
ከብዙ ዓመታት በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ሌሎች አማልክትን አመለኩ። በዚያን ጊዜ ኤልያስ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ነበር። እግዚአብሔር ኤልያስን ወደ ንጉሥ አክዓብ ሄዶ፦ “እኔን ማምለክ ትታችሁ ሌሎች አማልክትን ስላመለካችሁ፥ ለሚመጡት ዓመታት በእስራኤል ላይ ዝናብ አይዘንብም” ብሎ እንዲነግረው ላከው። በእርግጥም እግዚአብሔር እንዳለው ዝናብ ቆመ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስን “ከከተማ ርቀህ በአንድ ትንሽ ወንዝ አጠገብ ተደበቅ! ቁራዎች የምትበላውንም ምግብ ይዘውልህ እንዲመጡ አዛቸዋለሁ” አለው። ኤልያስም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ። እዚያም በየቀኑ ምግብ ቁራዎች ያመጡለት ነበር። በኋላም ደግሞ በሌላ ታአምር በራብ ወቅት ሁሉ የሚበቃውን ምግብ አገኘ።
ክፉው ንጉሡም በኤልያስ ተናድዶ በሁሉም ሀገር ቢያስፈልገውም፥ ሊያገኘው ግን አልቻለም።
Ravens Bring Food to Elijah
1 Kings 17
Many years later, the people of Israel worshipped other gods again. At that time, there was a man of God called Elijah. God sent him to King Ahab with the message, “Because you stopped worshipping me and instead worshipped idols, it will not rain in Israel for the next few years.” And indeed, it happened just as God said.
Then God told Elijah, “Go and hide beside a certain small river far away from other people! I will tell the ravens to bring you food.” So Elijah went to the place God told him to go. And there the ravens brought him food every day. Some time later, Elijah had enough to eat through yet another miracle. This way the prophet was cared for during the long drought.
The evil king was angry with Elijah and searched for him everywhere in the land, but he couldn’t find him.

ቁራዎቹ ምግብ ለኤልያስ ይዘው ሲመጡ
ምግብ ለኤልያስ እንዲሰጡ ቁራዎቹን ያዘዛቸው ማን ነው?
ያዘዛቸው እግዚአብሔር ነው።
ነቢዩ ዝናቡን እንዲቆም አላደረገም። ታዲያ፥ ለምን ዝናቡ ቆመ?
ሕዝቡ ሌሎች አማልክትን ስላመለኩ፥ እግዚአብሔር ዝናቡን አቆመ።
58. እውነተኛ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው
1ኛ ነገሥት 18
ዝናብ መዝነብ በቆመ በሦስተኛው ዓመት እግዚአብሔር ኤልያስን እንደገና ወደ ንጉሡ ላከው። ሄዶም ንጉሡን ከሌሎች አማልክት ነቢያት ጋር በአንድ ተራራ ላይ እንዲገናኙ ነገረው። ስለዚህ ሁሉም በዚያ ተራራ ላይ ተሰበሰቡ።
ከዚያም ኤልያስ ነቢያቱ ለአማልክታቸው ስጦታ እንዲያዘጋጁ፥ እርሱም ደግሞ ለእግዚአብሔር እንደሚያዘጋጅ ነገራቸው። ኤልያስም ለሕዝቡ “በስጦታው ላይ እሳትን የሚልክ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ በዚህ ይታወቅ!” አላቸው። ስለዚህ ኤልያስ ለእግዚአብሔር፥ እነርሱም ለራሳቸው አምላክ ስጦታ አዘጋጁ። በመጀመሪያ ነቢያቱ ቀኑን ሙሉ ወደ አማልክቶቻቸው ጸለዩ። ምንም እሳት ግን አልመጣም። በመጨረሻም ኤልያስ በስጦታው ላይ ውሃ አፈሰሰ። ከዚህ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ እሳት ወዲያውኑ ወረደ። ስጦታውን፥ ስጦታ የተቀመጠበትን እንጨት፥ እንዲሁም ድንጋይ እና ውሃውን በሙሉ አቃጠለ። ሕዝቡም ይህንን ካዩ በኋላ “እውነተኛ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው” ብለው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ከዚህም በኋላ ዝናብም እንደገና ዘነበላቸው።
The Real God
1 Kings 18
In the third year after it stopped raining, God sent Elijah to the king again. So he went and told the king to meet him on a certain mountain together with the prophets of other gods. And so everyone gathered on that mountain.
Then Elijah told the prophets to prepare a gift for their gods. He, on the other hand, would prepare one for God Almighty. Then Elijah said to the crowd, “Let it be clear now that the god who sends fire and burns the gift offered to him is the real God!” So Elijah prepared a gift for the God of Israel and the others prepared one for their gods. First, the other prophets prayed to their gods all day long. But no fire came down.
Finally, Elijah poured water on his gift and when he prayed to God Almighty, fire came down immediately. It burned up everything: the gift, the wood on which the gift had been put and even the stones and the water! When the people saw this, they said, “God is the only real god” and they worshipped him.
After this it started to rain again.

እግዚአብሔር ሕዝቡ እንደገና እንዲያመልኩት እሳት ሲልክ
እውነተኛ አምላክ የማን አምላክ ነው?
እውነተኛ አምላክ የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
59. ኤልያስ እና ኤልሳዕ
2ኛ ነገሥት 2
እግዚአብሔር ኤልሳዕን ከኤልያስ በኋላ ነቢይ እንዲሆን መረጠው። ኤልሳዕም ከኤልያስ ጋር ሄደ። የእርሱም ረዳት እና ተማሪ ሆነ። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ኤልያስ ከዚህ ዓለም የሚሄድበት ቀን ደረሰ። በዚያን ጊዜ አብረው በመሄድ ላይ እያሉ ድንቅ ነገር ሆነ። ይህም የእሳት ፈረሶች እና የእሳት ጋሪ በመካከላቸው ገብቶ ለያቸው። ኤልሳዕም እያየ ኤልያስ በጋሪው ሆኖ በነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ። ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ በኤልያስ ፋንታ ነቢይ ሆነ። እርሱም በእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ተአምራትን ለሕዝቡ ማድረግ ጀመረ።
Elijah and Elisha
2 Kings 2
God chose Elisha to become prophet after Elijah. And so Elisha went with Elijah. He assisted him and learned from him.
Some years later, the time arrived for Elijah to leave this world. The two men were traveling together, when something astonishing happened. Horses and a chariot of fire came between them and separated them. And Elisha saw how Elijah was taken on that chariot up to heaven in a whirlwind.
After this, Elisha became prophet in the place of Elijah. By God’s power, he started to do many miracles for the people.

ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲወሰድ
ኤልያስ ከዚህ ዓለም እንዴት ሄደ?
እግዚአብሔር ኤልያስን በእሳት ፈረስ ጋሪ ሆኖ በነፋስ ወደ ሰማይ ወሰደው።
60. የንዕማን መፈወስ
2ኛ ነገሥት 5
ንዕማን የሚባል የእስራኤል ጠላት የሆነች ሀገር የጦር መሪ ነበር። ይህ ሰው ግን ከባድ የቆዳ በሽታ ነበረበት። ስለ ነቢዩ ኤልሳዕም ከሰማ በኋላ፥ ለመፈወስ ወደ እስራኤል ሀገር መጣ። ኤልሳዕም ፈውስን ፈልጎ መምጣቱን ሲሰማ ወደ ቤቱ አስጠራው። ንዕማንም እቤቱ አጠገብ ሲደርስ፥ ኤልሳዕ መልእክተኛውን ልኮ፦ “ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ታጠብ! በዚያን ጊዜ ትፈወሳለህ” አለው። ንዕማንም ኤልሳዕ እንዳለው በወንዙ ታጥቦ ተፈወሰ። ከዚህም በኋላ ለኤልሳዕ ብዙ ውድ ስጦታዎችን ሊሰጠው ተመለሶ መጣ። ቢሆንም ኤልሳዕ ስጦታውን አልተቀበለም። ነገር ግን ሰራተኛው በጣም ተስገብግቦ ከንዕማን ኋላ ሮጦ በድብቅ ስጦታን ተቀበለ። በዚህ ምክንያት ልክ ንዕማን የነበረበት የቆዳ በሽታ ያዘው።
ንዕማን ከተፈወሰ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመለሶ የእስራኤልን አምላክ፥ እግዚአብሔርን ብቻ አመለከ።
Naaman’s Healing
2 Kings 5
A man called Naaman was the army commander of Israel’s enemies. He had a serious skin disease. When he was told about the prophet Elisha, he went to Israel to be healed. As soon as Elisha heard about his coming in search for healing, he had him come to his home. But when Naaman arrived, Elisha sent a messenger outside to tell him, “Go and wash yourself seven times in the River Jordan! Then you will be healed.”
Naaman washed himself like Elisha said and was healed. After that he returned to give Elisha many precious gifts. But Elisha didn’t accept anything. His servant Gehazi, however, was very greedy. He ran after Naaman, and secretly received a gift from him. Consequently he got the skin disease that Naaman had before.
After his healing, Naaman returned to his country and worshiped the God of Israel only.

ንዕማን ለመፈወስ ኤልሳዕን ሲጠይቅ
ንዕማንን ከበሽታው ያዳነው ማነው?
ያዳነው በኤልሳዕ ተጠቅሞ እግዚአብሔር ነው።
61. ኤልሳዕ እና ጠላቶቹ
2ኛ ነገሥት 6፥8-23
አንድ ጊዜ የእስራኤል ጠላቶች ነቢዩ ኤልሳዕን እና እስራኤልን ሊወጓቸው መጡ። እነርሱም እንደደረሱ ኤልሳዕ እንዲታወሩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ወዲያውኑ ሁሉም ማየት አቃታቸው። ስለዚህ ኤልሳዕ በቀላሉ እየመራቸው ወደ አንዲት ከተማ ወሰዳችው። በዚያም እንደገና ማየት እንዲችሉ ሲጸልይላቸው አይኖቻቸው ተከፈቱ። የእስራኤል ንጉሥ ይህንን ሲያይ “እንግደላቸው?” ብሎ ኤልሳዕን ጠየቀ። ኤልሳዕ ግን “አይሆንም፥ ምግብ አብልተን በሰላም እንዲሄዱ እንልቀቃቸው!” ብሎ መለሰለት። ስለዚህ የጠላት ወታደሮቹ ጥሩ ምግብ በልተው ወደ ሀገራቸው በሰላም ተመለሱ። ከዚህ በኋላ እነዚህ የእስራእሌል ጠላቶች ሊወጓቸው ተመልሰው አልመጡም።
Elisha and the Enemies
2 Kings 6:8-23
One time, the prophet Elisha and the people of Israel were attacked by enemies. When they arrived, Elisha prayed that God would make them blind. And immediately, they weren’t able to see anymore. As a result, it was easy for Elisha to lead them to a certain town. After they arrived there, he prayed that they would be able to see again and indeed their sight returned. When the King of Israel saw this, he asked Elisha, “Shall we kill them?” But Elisha answered, “Certainly not! We’ll give them food and then let them go home in peace.” Therefore, these soldiers received delicious food and then returned to their homeland in peace. After that, they never came back to attack.

ኤልሳዕ የታወሩ ጠላቶቹን ወደ ከተማ ሲወስዳቸው
እነ ኤልሳዕ ጠላቶቻቸውን እንዴት አሸነፉ?
እግዚአብሔር በኤልሳዕ በኩል አይናቸውን ስላሳወረ ነው።
እነ ኤልሳዕ ጠላቶቻቸውን ካሸነፉ በኋላ ምን አደረጉላቸው?
ጥሩ ምግብ አብልተው በሰላም ወደ ሀገራቸው ለቀቋቸው።
62. እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች አባረረ
2ኛ ነገሥት 6፥24-7፥20
አንድ ጊዜ ከእስራኤል ጠላቶች የተወሰኑ ወደ ሰማርያ መጥተው ከተማዋን ከብበው ለረጅም ጊዜ ቆዩ። ይህ በከተማዋ ለሚኖሩ ሰዎች እጅግ የመከራ ጊዜ ነበር። በዚህም ጦርነት ምክንያት ምግብ ስለጠፋ፥ በጣም ተራቡ።
በመጨረሻ* አራት የቆዳ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ግን ምግብ ፍለጋ ጠላቶቻቸው ወዳሉበት ቦታ ሄዱ። ሰዎቹም እዚያ ሲደርሱ፥ ጠላቶቹ የተውት* ብዙ ምግብ እና የተለያዩ ጠቃሚ ነገሮችን አገኙ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ለጠላቶቻቸው የብዙ ፈረሶች እና የወታደሮች ድምፅ በማሰማት አስደንግጦ አባሯቸው ስለነበር ነው። በዚያው ሌሊት አራቱ ሰዎች ይህንን መልካም ዜና ለሕዝቡ ለመናገር ወደ ከተማ ተመለሱ። ሕዝቡም ዜናው ከተረጋገጠ በኋላ፥ ከከተማይቱ ወጥተው የሚበሉትን እና ብዙ ሌሎች ነገሮችን ወሰዱ።
እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን አስድንግጦ በማባረር ከነበሩበት መከራ አዳናቸው።
God Chases Away Israel’s Enemies
2 Kings 6:24-7:20
One time, some of Israel’s enemies came to Samaria and surrounded the city for a long time. This was a time of great suffering for the people living in that city. Because of the war, they didn’t have enough to eat and were very hungry.
But finally, four men with a bad skin disease went out to the place where the enemies camped in search for food. When they arrived there, they found a lot of food and other things left behind. For God had caused their enemies to hear the sound of many horses and soldiers. By this, he had made them afraid and chased them away. That same night, the four men went back to the city to tell the good news to the people. When they found out that the message was true, the people rushed out of the city and took food and other things they needed.
God had scared and chased away their enemies. This way he saved them from their suffering.

አራቱ ሰዎች ጠላቶቻቸው ትተው የሄዱትን ነገሮች ሲያገኙ
የእስራኤል ሕዝብ ከጠላቶቻቸው እንዴት ነፃ ወጡ?
እግዚአብሔር ለጠላቶቻቸው የብዙ ሰራዊትን ድምፅ አሰምቶ በማስደንገጥ ስላባረረላቸው ነው።
63. ኢዮብ
ኢዮብ 1
ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚወድ ጥሩ እና ሀብታም ሰው ነበር። እግዚአብሔርም በእርሱ እጅግ ተደሰተ። ኢዮብም ሰውን ሁሉ የሚያክብር ጥሩ ተግባቢ ነበር። ሰባት ወንድ እና ሦስት ሴት ልጆች፥ እንዲሁም እጅግ ብዙ እንስሳት ነበሩት።
ለተወሰነ ጊዜ ሰይጣን ኢዮብን እንዲፈትነው እግዚአብሔር ፈቀደለት። ስለዚህ አንድ ቀን ሰይጣን ሊፈትነው መጣ። ወዲያውም ያለውን ሁሉ ከኢዮብ ላይ አጠፋበት። በዚህ ቀን ሰዎች በተደጋጋሚ እየመጡ መጥፎ ዜና ነገሩት። ስላጋጠመው መከራ ሁሉ ኢዮብ በጣም አዘነ። ሆኖም ግን “ሁሉን ነገር የሰጠኝ እግዚአብሔር ነው። መልሶ የወሰደውም እርሱ ነው። ስለዚህ አሁንም ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” አለ።
Job
Job 1
Job was a rich and good man who loved God. He was always friendly and treated everyone well. He had seven sons and three daughters, and also many, many animals. And God was very pleased with him.
God allowed Satan to test Job for a certain time. So one day, Satan came to test him and at once took away from him all that he had. On that day, one messenger after another came and brought him bad news. As a result, Job was very sad. Yet he said, “God gave me everything and he took it away again. Even now I will praise him!”

መልእክተኞቹ ለኢዮብ ስለደረሰበት መከራዎች በየተራ ሲነግሩት እና ኢዮብ ሲያለቅስ
ኢዮብ መጥፎ ዜና ሲሰማ ምን አለ?
ኢዮብ “ሁሉን ነገር የሰጠኝ፥ መልሶም የወሰደው እግዚአብሔር ነው“ ብሎ ክብር ለእግዚአብሔር ሰጠ።
64. የኢዮብ መከራ
ኢዮብ 2-42
ከዚህም በኋላ ኢዮብ በበሽታ እጅግ ተሰቃየ። ሚስቱም ይህንን ስቃይ ስታይ “እግዚአብሔርን ስድብ እና ሙት!” አለችው። ኢዮብ ግን “አልሳደብም፥ ከእግዚአብሔር ብዙ መልካም ነገሮች ተቀብለናል። ክፉ ነገር ሲመጣም መቀበል እንጂ፥ እርሱን መተው የለብንም” ብሎ መለሰላት። ኢዮብ የመጣበትን የመከራ ምክንያት ባይረዳም፥ መጥፎ ነገር በመናገር እግዚአብሔርን አላሳዘነም።
ከረጅም ጊዜ በኋላ የኢዮብ ከባዱ መከራ አበቃ። ሰይጣን እርሱን እንደገና እንዲጎዳው እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። ጤንነቱም ተመልሶለት በጣም ደህና ሆነ። እግዚአብሔርም እንደገና ሰባት ወንድ እና ሦስት ሴት ልጆችን ሰጠው። በተጨማሪም ከበፊቱ ይልቅ በብዙ እንስሳት ባረከው።
Job’s Suffering
Job 2-42
After that, Job became very sick and suffered a lot. When his wife saw his suffering, she said to him, “Curse God and die!” But Job answered her, “No I won’t, we have received many good things from God. We must also accept difficulties and not reject him!” Although Job didn’t understand the reason for his suffering, he didn’t speak against nor grieve God.
After a long time, Job’s terrible suffering stopped. God didn’t allow Satan to harm Job any longer. His health returned and God gave him seven sons and three daughters again. He also blessed him with more animals than he had had before.

ኢዮብ በታመመ ጊዜ ጓደኞቹ መጥተው ሲጠይቁት
ኢዮብ ችግር ባጋጠመው ጊዜ እግዚአብሔርን ተወ?
በፍጹም እግዚአብሔርን አልተወም።
65. ነቢዩ ዮናስ
ዮናስ 1-2
በእስራኤል ዮናስ የሚባል ነቢይ ነበር። አንድ ቀን እግዚአብሔር “ነነዌ ወደምትባል ከተማ ሄደህ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ክፉ ስራቸውን እንዲያቆሙ፥ ካልሆነ ግን እንደምቀጣቸው ንገራቸው!” ብሎ ላከው። ዮናስ ግን ወደ ነነዌ መሄድ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ በአንድ መርከብ ውስጥ ገብቶ ወደ ሌላ አቅጣጫ ተጓዘ። ዮናስም እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ኃይለኛ ነፋስ ላከበት። በመርከቡ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ችግሩ የደረሰባቸው በእርሱ ምክንያት እንደሆነ ተረዱ። ዮናስንም ማን እንደሆነ በጠየቁት ጊዜ፥ እርሱም “እኔ እግዚአብሔርን ስላልታዘዝኩ፥ ይህ ሆኗል። ወደ ውሃው ብትጥሉኝ ከባዱ ነፋስ ይቆማል” አላቸው። ዮናስም እንዳላቸው ካደረጉ በኋላ፥ ነፋሱ ቆመ። እግዚአብሔርም ትልቅ ዓሣ ዮናስን እንዲውጠው አዘዘ። ዮናስ ግን በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ በመጨረሻ* መጸለይ እና መዘመር ጀመረ።
The Prophet Jonah
Jonah 1-2
In Israel there was a prophet called Jonah. One day God said to him, “Go to the city called Nineveh and tell the people there to stop doing evil things! If they don’t, I will punish them!” But Jonah didn’t want to go there. He got into a ship and travelled in the other direction. Then God sent a storm, since Jonah had not obeyed him. The people in the ship finally realised that Jonah was the reason for the trouble. So when they asked him who he was, he told them, “All this is happening because I disobeyed God. But if you throw me into the water, the storm will stop!” And after they had done as Jonah suggested, the storm indeed stopped. Then God commanded a big fish to swallow Jonah. Inside the belly of the fish, Jonah finally started to pray and sing.

ዮናስ ወደ ነነዌ አልሄድም ብሎ ሲሸሽ
ዮናስን ለምን ትልቁ ዓሳ ዋጠው?
እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ነው።
66. ዮናስ በነነዌ
ዮናስ 3-4
ዮናስ ዓሣ ሆድ ውስጥ እያለ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ወሰነ። እግዚአብሔርም ይቅርታ አደረገለት። ስለዚህ ዓሣው ዮናስን ወደ ባሕሩ ዳር ወስዶ ለቀቀው። ከዚህ በኋላ ዮናስ እግዚአብሔር እንደፈለገው ወደ ነነዌ ሄደ። በዚያም ለነበሩት ሰዎች እግዚአብሔር የሰጠውን መልእክት ሰበከ። በስብከቱም ክፉ ስራቸውን እንዲተዉ፥ ካልሆነ ግን እንደሚቀጡ አስጠነቀቃቸው። ሕዝቡም መልእክቱን እንደሰሙ አግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው በፍጹም ልብ ለመኑት። ክፉ ስራቸውንም ወዲያውኑ አቆሙ። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ምሕረት አደረገላቸው።
እግዚአብሔር ሰዎችን በመቅጣት አይደሰትም። ሆኖም ግን ሰዎች እርስ በርሳቸው እና ከእርሱ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ይፈልጋል። ነቢይ የላከላቸውም ለዚህ ነው።
Jonah in Nineveh
Jonah 3-4
When Jonah was in the belly of the fish, he decided to obey God. And God forgave him. Then the fish took Jonah to shore and released him there. After this, Jonah went to the city of Nineveh, just as God wanted him to. There he passed on God’s message to the inhabitants. He warned them that they would be punished if they didn’t stop doing evil things. When the people heard his message, they sincerely begged God to forgive them. They stopped doing evil things to each other immediately. Therefore, God had mercy on them.
God does not enjoy punishing people. He rather wants them to live in peace with each other and with him. For this reason, he sent a prophet to the people.

የነነዌ ሕዝብ የዮናስን ማስጠንቀቂያ ሰምተው እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው ሲለምኑ
እግዚአብሔር ለማን ምሕረት አደረገ?
እግዚአብሔር ለዮናስ እና ለነነዌ ሕዝብ ምሕረት አደረገላቸው።
67. አስቴር እና የፋርስ ንጉሥ
አስቴር 1-5
አርጤክስስ የተባለው የፋርስ ንጉሥ እጅግ ኃያል ሰው ነበር። ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ባሉ ሀገራት ላይ ነገሠ። ሚስቱም ንግሥት አስቴር የምትባል እስራኤላዊት ነበረች።
ሐማ የተባለ ሰው የነጉሡ ዋና ሚኒስትር ነበር። የንግሥት አስቴር አጎት ስለማይሰግድለት፥ ሐማ እጅግ ተቆጣ። ከዚህ የተነሳ የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ ሊያጠፋ ከመንግሥት ደብዳቤ አጻፈ። እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ደነገጡ። ስለዚህ ክፉ ስራቸውን ትተው በጾም እና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። ንግሥት አስቴርም ወደ ነጉሡ ከመሄዷ በፊት ለሦስት ቀኖች ጾማ ጸለየች። ሕዝቡም ለአስቴር ጸለዩላት። ከዚያም በኋላ ለሕይወቷ አደገኛ ቢሆንም፥ ንጉሡ ሳይፈቅድላት ወደ እርሱ ሄደች። እርሱም ባያት ጊዜ ሳይቆጣት “አስቴር፥ ነይ! አትፍሪ! ምን ፈልገሽ መጣሽ?” አላት።
Esther and the King of Persia
Esther 1-5
Xerxes, the King of Persia, was extremely powerful. He reigned over all the countries from India to Ethiopia. His wife, Queen Esther, was from the people of Israel.
The main leader under King Xerxes was called Haman. Because Esther’s uncle did not bow down before Haman, Haman got very angry. He even ordered an official letter to be written to destroy all the Israelites and had the king authorise it. When the Israelites heard about this, they were terrified. Therefore, they stopped doing evil things, fasted and prayed together with Queen Esther to call on God for help. After that, Queen Esther risked her life by going to the king without his invitation. When the king saw her, he didn’t become angry. Instead, he said, “Come Esther, don’t be afraid! What can I do for you?“

ንጉሡ አስቴርን በመልካም ሁኔታ ሲቀበላት
የእስራኤል ሕዝብ መጥፎ ዜና ሲሰሙ ምን አደረጉ?
በጾም እና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
68. እግዚአብሔር እስራኤልን ከሐማ አዳነ
አስቴር 6-10
ንግሥት አስቴር ክፉውን ሚኒስትር ሐማን እና ንጉሡን በተከታታይ ሁለት ጊዜ እራት ጋበዘቻቸው። ከዚህም በኋላ አስቴር ንጉሡን እንዲያደርግላት የምትፈልገውን ጠየቀችው። እርሷም “ሕዝቤ በሐማ ተንኮል ምክንያት ሊጠፋ ተወስኗል፥ እባክህ አድነን” ብላ ለመነችው። ንጉሡም ልመናዋን ሰምቶ የእስራኤል ሕዝብ እንዳይጠፉ ትእዛዝ አስተላለፈ። ክፉው መሪ ሐማ ግን በሞት ተቀጣ። በእርሱ ቦታም የአስቴር አጎት ሚኒስትር ሆኖ ተሾመ።
ይህ ከጠላቶቻቸው የዳኑበት ቀን ለእስራኤላውያን የበዓል ቀን ሆነላቸው።
Haman’s plot – God saves Israel
Esther 6-10
Two times in a row, Queen Esther invited the evil leader Haman and the king for a meal. And so they ate together. After the second meal Esther told the king what she wanted him to do for her. She begged him and said, “Because of Haman’s evil plan it was decided to destroy my people. Please save us!“ The king listened to her and gave an order so the people of Israel would not be destroyed. But Haman, the evil leader, was sentenced to death. In his place, Esther’s uncle was appointed as leader.
The day on which the Israelites were saved from their enemies became a festival, which they celebrate every year.

አስቴር፥ ሐማ እና ንጉሡ አብረው እራት ሲበሉ
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከጥፋት ያዳናቸው እንዴት ነው?
ንጉሡ የአስቴርን ልመና ሰምቶ የእስራኤል ሕዝብ እንዳይጠፉ ትእዛዝ ስላስተላለፈ ነው።
69. ባቢሎን እስራኤልን* አሸነፈ
2ኛ ዜና 36፥14-21
እስራኤላውያን ኃጢያት ሲሰሩ፥ እግዚአብሔር በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ይልክላቸው ነበር። ስለዚህም ሕይወታቸውን ለማስተካከል ብዙ ዕድሎች ነበራቸው። እግዚአብሔር ክፉ ስራቸውን እንዲተዉ ብዙ ጊዜ ነቢያትን ልኮላቸው ነበር። እነርሱ ግን ኃጢያታቸውን ስላልተው፥ በመጨረሻ የባቢሎን ንጉሥ እንዲያሸንፋቸው ፈቀደ። ጠላቶቻቸውም ኢየሩሳሌም ከተማን እና ቤተ መቅደሳቸውን አፈረሱባቸው። እስራኤላውያንም በብዛት ወደ ባቢሎን ሀገር ተወሰዱ።
ቢሆንም እግዚአብሔር በምሕረቱ ብዛት፥ ሕዝቡን ሙሉ በሙሉ አላጠፋም። አሁንም ወደ እርሱ እንዲመለሱ ይፈልግ ነበር። ሆኖም እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርሚያስ በኩል ሕዝቡ ለሰባ ዓመታት በጠላቶቻቸው ጭቆና ሥር እንደሚሆኑ ተናገራቸው። ከዚያ በኋላ ግን ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ ሰጣቸው።
Babylon Conquers Israel
2 Chronicles 36:14-21
When the Israelites did wrong, God warned them repeatedly. So they had many chances to return to the right way. Time and again, God sent them prophets so that they would turn from their evil deeds. But because they didn’t listen, he finally allowed the King of Babylon to conquer them. Their enemies destroyed the city of Jerusalem and the temple. They took many of the Israelites to Babylon.
But because God is so merciful, he didn’t completely destroy his people. He still wanted them to turn to him again. Therefore, he told the people through the prophet Jeremiah that they would be captives for 70 years. And he promised them that they would return to their homeland after that.
ለሰባ ዓመታት
pic description
እስራኤላውያን ለምን ተሸነፉ?
የተሸነፉ በተደጋጋሚ እግዚአብሔርን ስላልታዘዙ ነው።
70. ዳንኤል እና ጓደኞቹ
ዳንኤል 1
የባቢሎን ንጉሥ መልካም ወጣቶችን ለሦስት ዓመት ትምህርት እንዲማሩ መረጠ። ተምረው ሲጨርሱ ከመካከላቸው በጣም ጎበዝ ተማሪዎችን አመካሪዎቹ ለማድረግ አቀደ። ለእነርሱም ንጉሡ ራሱ ከሚበላው ምርጥ ምግብ እና መጠጥ እንዲቀርብላቸውም አዘዘ።
ከተመረጡትም መካከል እስራኤላውያን የሆኑት ዳንኤል እና ሦስት ጓደኞቹ ነበሩ። እነርሱ ግን በእግዚአብሔር የተከለከለውን ምግብ አንበላም አሉ። ስለዚህ በንጉሥ ምግብ ፋንታ ጥራጥሬ ሊበሉ እና ውሃ ብቻ ሊጠጡ ስለወሰኑ ፈቃድ ጠየቁ። ከተወሰኑ ቀኖች በኋላ ከሌሎቹ ወጣቶች ይልቅ ሰውነታቸው አምሮበት ታየ። በተጨማሪም እግዚአብሔር ከሁሉ ይበልጥ ጥበብን እና እውቀትን ሰጣቸው። ስለዚህም ንጉሡ የቅርብ አማካሪዎቹ እንዲሆኑ መረጣቸው።
Daniel and His Friends
Daniel 1
The King of Babylon chose some clever young men to receive special training for three years. It was his plan to select the best of them to become his advisors afterwards. The king ordered that these young students were served the same delicious food and drink that he ate and drank himself.
Daniel and his three friends were among the ones who were chosen for this training. They were Israelites. During their training, they didn’t want to eat food that God had forbidden. Therefore, they asked for permission to eat vegetables and drink water instead of the king’s food. And after some time, they looked healthier than the other young men. Additionally, God gave them more wisdom and knowledge than all the others. So after their training, the king chose them to become his personal advisors.

ዳንኤል እና ሦስቱ ጓደኞቹ የንጉሡን ምግብ አንበላም ሲሉ
ዳንኤል እና ጓደኞቹ ከሌሎቹ ይልቅ በጥበብ የበለጡት ለምንድን ነው?
በጥበብ የበለጡት እግዚአብሔርን ስለታዘዙ እና ስለታመኑ ነው።
71. የንጉሡ አስቸጋሪ ሕልም
ዳንኤል 2
አንድ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ሕልምን አየ። የሕልሙም ትርጉም ስላልገባው እጅግ ተጨነቀ። ስለዚህ ሕልምን መተርጎም ይችላሉ የተባሉ ሰዎችን ጠርቶ “ያየሁትን ሕልም እና ትርጉም ንገሩኝ! ሁለቱንም ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ ግን፥ ሞት ይፈረድባችኋል” አላቸው። ሆኖም ሁሉም የንጉሥን ሕልም እና ትርጉም ሊያውቁ አልቻሉም።
ዳንኤል እና ጓደኞቹ ይህንን ሲሰሙ፥ እግዚአብሔር ሕልሙን እንዲገልጥላቸው በጾም እና በጸሎት ጠየቁ። እግዚአብሔርም ሕልሙን እና ፍቺውን ለዳንኤል ነገረው። ንጉሡ ያየው ሕልም ወደፊት ስለሚመጡት መንግሥታት እንደሆነ አስረዳው።
The King’s Mysterious Dream
Daniel 2
One night the King of Babylon had a dream. He was very worried, because he didn’t know what it meant. So he called the men that were said to understand such matters and commanded, “Tell me both my dream and its meaning! If you’re not able to do that, you will be sentenced to death.” But none of them was able to.
When Daniel and his friends heard about it, they fasted and prayed that God would reveal the dream to them. And indeed, God told Daniel the dream and its meaning. He helped him to understand that the king’s dream was about future kingdoms.

ዳንኤል ለንጉሡ ስላየው ሕልም ሲነግረው
ሕልሙን እና ፍቺውን ለዳንኤል ያሳየው ማን ነው?
ያሳየው እግዚአብሔር ነው።
72. የወርቁ ሐውልት እና ሦስቱ ሰዎች
ዳንኤል 3
አንድ ቀን የባቢሎን ንጉሥ እርሱን የሚመስል ትልቅ የወርቅ ሐውልት አሰራ። በመንግሥቱም ያሉትን መሪዎች ሁሉ ጠርቶ ለምስሉ እንዲሰግዱ አዘዛቸው። ሦስቱ የዳንኤል ጓደኞች ግን ለወርቁ ሐውልት ለመስገድ ፈቃደኛ አልነበሩም። ምክንያቱም ሊሰገድለት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ስላወቁ ነው። ንጉሡ ይህንን ሲሰማ በጣም ተናደደ። ከዚህ የተነሳ ወደ ትልቅ እሳት እንዲጣሉ አደረገ። ሆኖም ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ስለመጣ፥ እሳቱ ምንም አላቃጠላቸውም። ንጉሡም ይህንን ሲያይ “እንዴ! እንዴ! አራት ሰዎች በእሳት ሲመላለሱ እየያሁ ነው። ከመካከላቸው አንዱ የእግዚአብሔር መልአክ ይመስላል” አለ። ውዲያውም ሦስቱ ሰዎች ከእሳቱ እንዲወጡ ጠራቸው። ከዚያም “እንደ እስራኤል አምላክ ያለ ትልቅ አምላክ የትም የለም” አለ። ንጉሡም ሰዎች ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤልን አምላክ፥ እግዚአብሔርን በፍጽም እንዳይሰድቡ ሕግ አወጣ።
The Golden Statue and the Three Men
Daniel 3
One day the King of Babylon commanded a big golden statue to be made that looked like him. When it was finished, he called all the leaders of his kingdom and told them to bow down and worship the statue. But Daniel’s three friends refused to bow down for they knew that only the God of Israel was worthy to be worshipped.
When the king heard this, he became very angry. So he had them thrown into an enormous fire. But God’s angel came and protected them, so the fire did not burn them. When the king saw what happened, he said, “What on earth is going on here? I see four people walking about in the fire. And one of them looks like an angel!” He quickly called the men to come out and said, “No other god is as great as the God of Israel.” He then made a law saying that from now on no one should ever insult the God of Israel.

እግዚአብሔር ሦስቱን ሰዎች ከእሳት ሲያድናቸው
የዳንኤል ወዳጆች ለወርቁ ሐውልት ለምን አልሰገዱም?
ሊሰገድለት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ስላወቁ ነው።
73. ዳንኤል መጸለዩን አላቆመም
ዳንኤል 6
ዳንኤል ንጉሡን በታማኝነት ስለሚያገለግለው ይወደው ነበር። ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣኖች ግን በዳንኤል ቀኑበት። ዳንኤልም ሁልጊዜ የሚጸለይ ሰው እንደሆነ ያውቁ ነበር። ስለዚህ ወደ ንጉሡ ሄደው “ማንም ሰው ለሠላሳ ቀኖች ወደ አምላኩ እንዳይጸልይ፥ ከጸለየ ግን አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ ይጣል” የሚል ሕግ አወጡ።
ዳንኤል ግን ሁልጊዜ እንደሚያደርገው በየቀኑ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ። ባለሥልጣኖቹም ዳንኤልን ሲጸልይ አዩት። በዚያን ጊዜ በፍጥነት ወደ ንጉሡ ሄደው ያዩተን ነገሩት።
Daniel Keeps Praying
Daniel 6
The king loved Daniel, because he served him faithfully. For this reason, some leaders became jealous of Daniel. They knew that he was a man who prayed every day. Therefore, with the king’s permission, they made a new law. It said: “Nobody is allowed to pray to any god for thirty days. But if someone does pray, he will be thrown into the pit with lions.”
Daniel however kept praying to God as usual. And when the leaders saw him pray, they quickly went to the king and reported it to him.

ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ
ዳንኤል የጸለየው ወደ ማን ነው?
ዳንኤል የጸለየው ወደ እግዚአብሔር ነው።
74. ዳንኤል እና አንበሶቹ
ዳንኤል 6
ንጉሡ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር እንደጸለየ ሲሰማ፥ እርሱን ይወደው ስለነበር፥ በጣም አዘነ፤ ደግሞም ተጨነቀ። ሕጉ ግን የማይቀየር ስለሆነ፥ ንጉስ ሊረዳው አልቻለም።
ስለዚህ ዳንኤልን አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። በመጨረሻ ነጉሡ ለዳንኤል “ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ!” ብሎት ወደ ቤቱ ተመለሰ።
በሚቀጥለው ቀን በማለዳ ንጉሡ ወደ ጉድጓዱ በፍጥነት ሄዶ “ዳንኤል፥ አምላክህ አዳነህ?” ብሎ ጮኸ። ዳንኤልም “አዎን፥ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘግቶ አዳነኝ” ሲል መለሰለት። ንጉሡም በጣም ደስ አለው። ወዲያውኑም ወደ ነበረበት ትልቅ ሥልጣን እንዲመለስ አደረገ። ንጉሡም ሰዎች ሁሉ ኃያል የሆነውን የዳንኤልን አምላክ፥ እግዚአብሔር ብቻ እንዲያከብሩ አዘዘ።
Daniel and the Lions
Daniel 6
When the king heard that Daniel had prayed to God, he was very worried and sad, because he loved Daniel. But he was not able to help him since the law could not be changed. Therefore, they threw Daniel into the pit with lions. Before the king went home he said to Daniel, “May the god that you always worship rescue you!”
Early the next morning the king got up, quickly went to the pit and shouted, “Daniel, did your God save you?” And Daniel answered, “Yes, my God sent his angel, shut the mouths of the lions and saved me.” The king was, of course, very happy. He immediately returned Daniel to his high position. Additionally, he commanded that everyone must be in awe of Daniel’s powerful God.

መልአኩ ዳንኤልን ከአንበሶች ሲጠብቅ
እግዚአብሔር ዳንኤልን ከአንበሶች ለማዳን ማንን ላከ?
ዳንኤልን ለማዳን መልአኩን ላከ።
75. ኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ተሰራ
መጽሐፍ ነህምያ + ዕዝራ
በባቢሎን ሀገር ተማርከው ከተወሰዱት እስራኤላውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። እነርሱም ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስ እንደገና መስራት ጀመሩ። ሆኖም ግን ጠላቶቻቸው እንዳይሰሩ ስለከለከሏቸው፥ ተስፋ ቆርጠው ትተውት ነበር። እግዚአብሔር ግን ቃሉን በነቢያቱ በሐጌ እና በዘካርያስ ልኮ አበረታታቸው። ከዚያም ሕዝቡ በፍጥነት ቤተ መቅደሱን ሰርተው ጨረሱ።
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ደግሞ ነህምያ የተባለ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ የፈረሰውን የከተማዋን አጥር ለመስራት ወሰነ። ሕዝቡም ከነህምያ ጋር ለመስራት ተስማሙ። ያደረጉትን መጥፎ ሰራዎቻቸውንም አቆሙ። ከዚያም በአንድነት መስራት ጀመሩ። ግማሾቹ ሰዎች አጥሩን ሲሠሩ፥ ሌሎቹ ደግሞ ከተማዋን ይጠብቁ ነበር። እግዚአብሔርም ስለረዳቸው፥ በኀምሳ ሁለት ቀኖች የከተማዋን ዙሪያ የድንጋይ አጥር በሙሉ ሰርተው ጨረሱ። በዚህም ሕዝቡ እጅግ ደስ አላቸው። እግዚአብሔርንም በዝማሬ አመሰገኑ።
Jerusalem Rebuilt
Books: Ezra + Nehemiah
When the first Israelites returned from exile to their land, they started to rebuild the temple that had been destroyed. But because their enemies troubled them, they were discouraged and stopped. So God sent the prophets Zechariah and Haggai to encourage them to continue rebuilding his house. After that, they quickly finished building it.
A few years later, a man called Nehemiah came to Jerusalem and decided to rebuild the city walls that had been destroyed. The people there agreed to join him. They stopped doing evil things and started to work together in unity. While half of the people worked on rebuilding the wall, the others guarded the city. And because God helped them, they finished building the whole city wall in 52 days. Then the people celebrated and thanked God with songs.

ሕዝቡ የከተማዋን አጥር ከጠላቶቻቸው እየጠበቁ ሲሰሩ
ሕዝቡ የኢየሩሳሌምን አጥር በፍጥነት እንዴት ሰርተው ጨረሱ?
በፍጥነት የጨረሱት እግዚአብሔር ስለረዳቸው እና በአንድነት ስለሰሩ ነው።
76. የዕዝራ ትምህርት
ነህምያ 8-10 እና ዕዝራ 8
በሌላ ጊዜ ደግሞ ዕዝራ የተባለ ካህን ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል የማስተማር ችሎታ ነበረው። እስራኤላውያንን እንዴት ለእግዚአብሔር መኖር እንዳለባቸው አስተማራቸው። ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሕዝቡ በቀላሉ ትምህርቱን ማስተዋል እንዲችሉ ረዷቸው።
አንድ ጊዜ ደግሞ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ሕግ ሲሰሙ ተስፋ ስለቆረጡ፥ ግብዣ እንዲያደርጉ ነገራቸው። በተጨማሪም እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ያደረገላቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ በደንብ እያስታወሱ አመሰገኑ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ቃል ገቡ።
በዚህ መንገድ ነህምያ እና ዕዝራ አብረው ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን ሕዝብ አገለገሉ።
Ezra’s Teaching
Nehemiah 8-10 and Ezra 8
At a certain time, a priest called Ezra also returned from Babylon to Jerusalem. He had the skill to teach the word of God. So he taught the Israelites how to live their lives with God. And some men assisted him, so that the people could easily understand his teaching.
One time, when the people were listening to the law of God, they were discouraged and wanted to give up. So Ezra told them to celebrate a feast. At the celebration they consciously remembered all the good things God had done for them in the past and thanked him. And afterwards they promised to keep God’s laws.
This is how Nehemiah and Ezra together served the people who had returned to Jerusalem.

ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙ
ሕዝቡ ምን አስታወሱ?
እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ያደረገላቸውን መልካም ነገሮችን ሁሉ አስታወሱ።
ኢሳይያስ 9 + 11 + 53 ወዘተ
በእስራኤል ሀገር ኢሳይያስ የተባለ አንድ ነቢይ ነበር። እግዚአብሔር በእርሱ በኩል የእስራኤልን ሕዝብ በተደጋጋሚ አስጠነቀቀቸው፥ ደግሞም አበረታታቸው። እስራኤላውያን ግን እንደ አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን አልታዘዙም። ኢሳይያስም ለወደፊት ከኃጢአታቸው ንጹሕ የሚያደርግ አዳኝ እንደሚመጣ ነገራቸው። በተጨማሪም “ይህ አዳኝ ይጠብቃችኋል፥ ይፈውሳችኋል፥ እንዲሁም ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅ እንዲሆኑ ያደርጋል” በማለት ስለ ኢየሱስ ትንቢት ተናገረ።
ይህንን ትንቢት የተናገረው ኢየሱስ ከመወለዱ ከ700 ዓመታት በፊት ነበር።
A Prophecy About Jesus
Isaiah chapter 9, 11, 53 etc.
There was a prophet in Israel called Isaiah. Through him, God repeatedly both warned and encouraged his people. But just like Adam and Eve, the people didn’t obey God. Isaiah told them about a Saviour who would come in the future and take away their sins. He prophesied about Jesus when he said, “This Saviour will protect you, heal you and restore your friendship with God.”
Isaiah prophesied thist already 700 years before Jesus was born.
700
ዓመታት


በታሪክ 49-77 ፈልግ፡
77. ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት