104-127 የኢየሱስ አገልግሎት ቀጠለ
More of Jesus’ Ministry

ታሪኮችን ለመክፈት ከዚህ በታች የምትፈልጉትን ተጫኑ
104. ማርያም እና ማርታ
ሉቃስ 10፥38-42
አንድ ቀን ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር አንድን ቤተሰብ ጎበኙ። እነርሱም ማርታ፥ እህቷ ማርያም እና ወንድሟ አልዓዛር ነበሩ። በዚያን ጊዜ ማርያም ተቀምጣ ኢየሱስ የሚያስተምረውን ስትሰማ፥ ማርታ ግን እንግዶችን ለማስተናገድ በስራ ትተጋ ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ማርታ ኢየሱስን “እባክህ፣ እህቴን እንድትረዳኝ ንገራት” አለችው። ኢየሱስ ግን “ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ። ማርያም ግን እኔን በመስማቷ ከሁሉ የሚበልጠውን ነገር እያደረገች ነው” ብሎ መለሰላት።
Mary and Martha 
Luke 10:38-42
One day Jesus and his disciples visited Martha, her sister Mary and their brother Lazarus. Martha worked hard to serve the guests while Mary was sitting and listening to Jesus’ teaching.
After some time Martha said to Jesus, “Please, tell my sister to help me.” But Jesus responded, “Martha, you are worried about many things. But Mary is doing what matters most by listening to me.”

ማርታ እንግዶቿን ስታስተናግድ እና ማርያም ደግሞ የኢየሱስን ትምህርት ስትሰማ
እንግዶችን ማስተናገድ እና ስራ መስራት መልካም ቢሆንም፥ ከዚህ የሚበልጠው ግን ምንድን ነው? 
ከኢየሱስ ጋር መሆን እና ትምህርቱን መስማት ይበልጣል።
105. ብዙ ሀብት ሰብስቦ የሞተ ሰው 
ሉቃስ 12፥16-21
ኢየሱስ ስለ ሀብት እንዲህ ሲል አስተማረ፡
– በጣም የተሳካለት አንድ ሀብታም ሰው ነበር። ማስቀመጫ ቦታ እስከማይበቃው ድረስ ብዙ ምርት አገኘ። ስለዚህ የምርት ማስቀመጫ ቤቶቹን አፈርሶ ከበፊት የበለጠ ትላልቅ አድርጎ ሰራቸው። ለራሱም “ከዚህ በኋላ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ ስላዘጋጅሁ፥ ለብዙ አመታት እየበላሁ እና እየጠጣሁ በደስታ እኖራለሁ” አለ። ሀብታሙ ሰው ግን በዚያች ሌሊት ሞተ። ስለዚህ ያለው ንብረት ለእርሱ ሊሆን እና ሊጠቅመው አልቻለም። ይህ ሀብታም ሰው በሰማይ ምንም ሀብት ሳያስቀምጥ ሞተ።
The Man with the Huge Storage 
Luke 12:16-21
Jesus taught about wealth with this story:
There was an incredibly successful man. Since he had such excellent harvests, he tore down his storehouses and built much bigger ones instead. Afterwards he said to himself, “Since I have prepared so well for the future, I will have plenty for many years to come. I will enjoy life.” But the rich man died that very night. Therefore, his possessions were of no use to him. He had not stored any wealth in heaven before he died.

በከንቱ ብዙ ሀብት የሰበሰበ ሰውየው
ስለራሳችን ብቻ እያሰብን መኖር ጥሩ ነው? 
አይ፥ ጥሩ አይደለም። ለሌሎችም ሰዎች ማሰብ አለብን።
እግዚአብሔርን መውደድ እና ለሌሎች ሰዎች ካለን ሀብት በፍቅር እያካፈልን መኖር አይሻልም? 
አዎን፥ ይሻላል።
106. ኢየሱስ አንዲት በሽተኛ ፈወሰ
ሉቃስ 13፥10-17
ኢየሱስ በሰንበት ምኵራብ በሚባለው በእግዚአብሔር ቤት ያስተምር ነበር። እዚያም ለአሥራ ስምንት አመታት የታመመች አንዲት ሴት አየ። ይህችም ሴት ከሰይጣን መንፈስ የተነሳ ቀጥ ብላ መቆም ወይም መራመድ አትችልም ነበር። ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እጁን በእርሷ ላይ አድርጎ ፈወሳት። ወዲያውም ጀርባዋ ቀጥ ስላለ፥ በትክክል መሄድ ቻለች። እግዚአብሔርንም ከበሽታዋ ስለፈወሳት በጣም አመሰገነች። የእግዚአብሔር ቤት መሪ ይህንን ፈውስ ባየ ጊዜ “በሰንበት ለምን ትፈውሳለህ? በሰንበት ስራ መስራት እንደማይፈቀድ አታውቅም?” ብሎ ተቆጣው። ኢየሱስም “በሰንበት እንሰሳው ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ቢያየው የማያወጣ ማንም የለም። እንዲሁም ይህች ለአሥራ ስምንት አመታት ሰይጣን ያሰራትን ሴት ከእስራቷ ልፈታት አያስፈልጋትም? ያስፈልጋታል” አለው።
ኢየሱስ በፍቅር የተሞላ ስለሆነ፥ ስራ በማይሰራበት ቀን እንኳን እንደዚህች ሴት የሚጨነቁትን ሰዎች ይረዳል።
Jesus Heals a Crippled Woman
Luke 13:10-17
On a Sabbath Jesus was teaching in a synagogue, which is a house of God. There he saw a woman who had been crippled for 18 years. She was not able to stand up straight. Evil spirits had caused her to be like this. But Jesus called her to him, put his hand on her body, and healed her. Immediately her back straightened and she was able to walk normally. Can you imagine how gratefully she praised God?!
But when the leader of the synagogue saw that Jesus healed her, he got angry. He said to him, “Why do you heal on the day of rest? Don’t you know that it is not permitted to do work on such a day?” Jesus responded, “If one of your animals fell into a hole on a day of rest, you surely would rescue it! Is it not much more important to free this woman who has been bound by Satan for 18 years? Of course it is!”
Because Jesus is filled with so much love, he helps people who are in trouble just like this woman, even on the day of rest.

ኢየሱስ በሰንበት አንዲትን ሴት ሲፈውስ
ሰዎችን ከሰይጣን መንፈስ ነፃ ማውጣት የሚችል ማን ነው?
ከሰይጣን መንፈስ ነፃ ማውጣት የሚችለው ኢየሱስ ነው።
107. የእግዚአብሔር ግብዣ
ሉቃስ 14፥15-23
ኢየሱስ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ስለመጥራት እንዲህ ሲል አስተማረ፡-
አንድ ታላቅ ሰው ትልቅ ግብዣን አዘጋጀ። ሰዎችንም ወደ ግብዣው እንዲጠራ ሰራተኛውን ላከው። ነገር ግን ከተጠሩት አንዱ “መሬት ስለገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝና መምጣት አልችልም” አለ። ሁለተኛው ደግሞ “በሬዎች ስለገዛው እነርሱን ላለማምድ እሄዳለሁ። ይቅርታ አድርግልኝ፥ መምጣት አልችልም” አለ። ሌላኛውም “አሁን ሚስት ስላገባሁ፥ መምጣት አልችልም” ብሎ መለሰለት። እንደዚህ ሁሉም የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ቀሩ። ታላቁም ሰው እነዚህን መልሶች ሲሰማ በጣም ተቆጣ። ወዲያውም በእነርሱ ቦታ ድሆችን፥ አንካሶችን እና ዐይነ ስውሮችን ወደ ግብዣው አስጠራ። እነርሱም እሺ ብለው ወደ ግብዣው መጡ።
God’s Great Feast
Luke 14:15-23
Jesus told this story to teach about God’s invitation into his Kingdom:
An important man prepared a feast and sent out his servant to invite people for the meal. But one of the men invited responded, “I have just bought some land. I have to go look at it. I cannot come.” The second man said, “I have just bought some oxen. I have to see to it that everything is okay. Please, excuse me. I cannot come.” Yet another one answered “I just got married. I cannot come!” In this way they all made excuses and didn’t come. When the great man heard these answers, he became very angry with those he had invited. He quickly had his servants call poor, crippled and blind people in their place. They accepted his invitation and came to the feast.

ድሆች እና በሽተኞች ወደ ግብዣው ሲመጡ
እንደ ታላቁ ሰው ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ወደ መንግሥቱ ይጠራል። እናንተስ ይህንን ግብዣ ተቀብላችሁ መምጣት ትፈልጋላቸሁ?
108. ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው
ዮሐንስ 10
ኢየሱስ በፍቅር የተሞላ እውነተኛ እረኛ ነው። ድምፁን ሰምተን ወደ እርሱ ከመጣን በጎቹ ነን። በየስማችን ያውቀናል ደግሞም ይጠራናል። እርሱን እንጂ ሌላ እረኛ አንከተልም። ይህ መልካም እረኛ ወደ ለምለም ቦታ ይመራናል። አውሬ ሲመጣብንም ይጠበቀናል እንጂ አይሸሸም። እርሱ ክፉን ሁሉ ያሸነፋል። ለበጎቹ ለመሞት እንኳን ዝግጁ ነው። ከመንጋው መስረቅ የሚችል ማንም የለም። ስለዚህ እውነተኛ መልካም እረኛ እርሱ ብቻ ነው። እርሱን ስንከተል ነው የዘላለም ሕይወት የሚኖረን።
Jesus, the Good Shepherd
John 10
Jesus is the good shepherd who truly loves us. When we hear his voice and come to him we are his sheep. He knows us and calls us by our name. We follow him and no other shepherd. This good shepherd leads us to green pastures. And when a dangerous animal comes to attack us, he does not run away, but protects us. He is victorious over all evil. He even gave up his life for his sheep. Nobody can steal from his flock. Therefore, he is the only good shepherd. When we follow him, we have eternal life.

ኢየሱስ መልካም እረኛ ሆኖ ከአደጋ በጎቹን ሲጠብቅ
የኢየሱስ በጎች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
የኢየሱስን ድምፅ ሰምተን ስንከተለው ነው።
109. የአባቱን ቤት ትቶ የሄደው ልጅ
ሉቃስ 15፥11-19
ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር እንዲህ ሲል በዚህ ታሪክ አስተማረ፡-
አንድ አባት ሁለት ልጆች ነበሩት። አንድ ቀን ታናሹ ልጅ አባቱን “የእኔን የሀብት ድርሻ ስጠኝ እና ልሂድ!” አለው። አባቱም በጥያቄው ቢያዝንም፥ ከሀብቱ ድርሻውን ሰጠው። ከዚያም ልጁ የተሰጠውን ገንዘብ ይዞ ወደ ሌላ አገር ሄደ። እዚያም ገንዘቡን በሙሉ አባክኖ ከጨረሰ በኋላ፥ የሚበላው አጣ። ስለዚህ በአንድ ገበሬ ቤት የዐሣማዎች እረኛ ሆኖ መስራት ጀመረ። እዚያም እያለ የዐሣማዎቹን ምግብ መብላት እስኪፈልግ ድረስ በጣም ተራበ። ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ጀመረ። በመጨረሻም ከዚህ ችግር የሚወጣበት አንድ ጥሩ ሐሳብ መጣለት።
The Son Who Left His Father
Luke 15:11-19
Jesus taught how great God’s love is with this story:
A father had two sons. One day the younger one said to his father, “Give me my inheritance, I want to leave.” The father was grieved by his request, but he gave him his share. The son took the money and went to another country. There he wasted everything he owned. After that, he had nothing to eat. So he started to work for a farmer, taking care of his pigs. He was so hungry that he even longed to eat the pigs’ food. Then he started to think about a possible solution. And eventually he had an excellent idea.

ልጁ ድርሻውን ወስዶ የአባቱን ቤት ትቶ ሲሄድ
ታናሹ ልጅ ምን ጥፋት ሰራ?
ጥፋቱ ከአባቱ ቤት መሄዱ እና ሀብቱን በሙሉ አባክኖ መጨረሱ ነው።
110. ከአባቱ ቤት የሄደው ልጅ መመለስ
ሉቃስ 15፥20-24
በመጨረሻም ልጁ በጣም ስለራበው እንደዚህ ብሎ አሰበ: “በአባቴ ቤት ለሰራተኞች ጭምር የሚሆን በቂ ምግብ ስላለ፥ ወደዚያ መመለስ አለብኝ። አባቴንም እንደሰራተኞቹ አድርጎ እንዲቀበለኝ እለምነዋለሁ” በማለት ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ። አባቱ ገና ከሩቅ ባየው ጊዜ አዘነለት። ወደ እርሱም ሮጦ በደስታ አቅፎ ተቀበለው። ልጁም “እባክህ፥ አጥፍቻለሁና እንደ ሰራተኛህ ሆኜ እንድኖር ፍቀድልኝ። ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ለመሆን ብቁ አይደለሁም” አለው። አባቱ ግን ልጁ በመመለሱ ደስ ስላለው፥ በፍጥነት የሚያምር ልብስ እና ቀለበት ሰጠው። የልጁንም መመለስ ለማክበር በሬን አርዶ ትልቅ ግብዣ አደረገለት።
The Son’s Return
Luke 15:20-24
Because the son was so hungry, he finally said to himself, “My father’s workers are better off than I am, they’ve got enough food to eat. I must return to my father. I will beg him to accept me as one of his servants.” Then he returned home. His father saw him coming from a distance and was filled with compassion. Full of joy he ran towards him and embraced him. At this, the son said to him, “I have done wrong. Please allow me to stay with you as your servant! I am not worthy to be your son.” The father, however, was so delighted that his son had returned that he quickly gave him beautiful clothes and a ring. He ordered an ox to be slaughtered, and they celebrated the return of his son with a great feast.

አባቱ ከቤት የሄደበት ልጁ ሲመለስ በደስታ ሲቀበለው
ልጁ ሲመለስ አባቱ ምን አደረገ?
አበቱ በደስታ አቅፎ ከተቀበለው በኋላ፥ አዲስ ልብስ እና ቀለበት ሰጥቶት ታላቅ ግብዣ አደረገለት።
111. አልዓዛር እና ሀብታሙ ሰው
ሉቃስ 16፥19-31
ኢየሱስ አንድን ታሪክ ተጠቅሞ እንዲህ ሲል አስተማረ፦
አልዓዛር የሚባል አንድ በጣም ድሀ ሰው ነበር። ከአንድ ሀብታም ሰው ቤት አጠገብ ተኝቶ ነበር። የሀብታሙን ሰው እርዳታ ቢጠብቅም፥ እርሱ ግን አልረዳውም። አልዓዛር ውሾች መጥተው ቁስሎቹን እስኪልሱ ድረስ ተሰቃየ። ሀብታሙ ሰው ግን በነበረው ሀብት ለራሱ ብቻ እየተደሰተ ይኖር ነበር።
አንድ ቀን አልዓዛር ሲሞት ወደ ጥሩ ቦታ ተወሰደ። እዚያም ከነ አብራሃም ጋር በታላቅ ደስታ መኖር ጀመረ። ትንሽ ቆይቶም ሀብታሙ ሰው ደግሞ ሞተ። እርሱ ግን በጣም አስከፊ እና ስቃይ ወዳለበት ቦታ ተወሰደ። ሰውየው ስለተሰቃየ አልዓዛርን መጥቶ ስቃዩን እንዲቀንስለት አብራሃምን ጠየቀ። አብራሃም ግን “ይህንን እዚህ ማድረግ የማይቻል ነገር ነው” ብሎ መለሰለት። ሀብታሙ ሰው ከመሞቱ በፊት እግዚአብሔር ደስ የሚለውን ነገር ቢያደርግ ኖሮ፥ ወደ ጥሩው ቦታ ይወሰድ ነበር።
Lazarus and the Rich Man
Luke 16:19-31
One time Jesus used this story to teach:
There was a really poor man called Lazarus. He used to sleep in front of a rich man’s house and in vain hoped for his help. Dogs came and licked his wounds. That’s how much he suffered. The rich man, however, selfishly enjoyed his good life and didn’t care about Lazarus.
One day Lazarus died and ended up in a good place beside Abraham. There he lived in great joy. Some time later also the rich man died. But he ended up in a horrible place, where he suffered a lot. He suffered so much, that he asked Abraham to send Lazarus over to relieve his misery. But Abraham answered him, “That is not possible here.” If the rich man had lived a life pleasing to God, he also would have ended up in the good place.

አልዓዛር ከሀብታሙ ምግብ ሲጠብቅ እና ውሾች ቁስሉን ሲልሱ
አልዓዛር ከሞተ በኋላ ምን ሆነለት?
ወደ ጥሩ ቦታ ተወሰዶ በታላቅ ደስታ ኖረ።
112. አመስጋኙ ሰው
ሉቃስ 17፥11-19
ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በጉዞ ላይ እያለ፥ አሥር የቆዳ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሩቅ አዩት። እንደዚህ ዐይነት በሽተኛ በሕዝብ መካከል መኖር አይችልም ነበር። እነዚህ አሥር ሰዎች “ኢየሱስ፥ እባክህ ፈውሰን!” ብለው ጮኹ። ኢየሱስም “ወደ ካህን ሄዳችሁ ከበሽታው እንደዳናችሁ ያረጋግጥላችሁ!” ብሎ ነገራቸው። እርሱም ይህንን ያለው ወደ ካህን በመሄድ ላይ እያሉ እንደሚፈወሱ ስላወቀ ነው። እነርሱም ኢየሱስ እንዳላቸው ሄዱ። በመንገድም ላይ እያሉ ተፈወሱ። መዳናቸውንም ለካህን አሳዩ። ይህም በዚያን ጊዜ ሰዎች ከቆዳ በሽታ መዳናቸውን የሚያረጋግጡበት የተለመደ ስርአት ነበር።
ከተፈወሱትም ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ወደ ኢየሱስ ተመልሶ በጣም አመሰገነው። ይህ ሰው እስራኤላዊ እንኳን አልነበረም። ኢየሱስም “በሰላም ወደ ቤትህ ሂድ! በእኔ ስላመንህ ድነኃል” አለው። ደግሞም “የፈውስኳቸው 10 ሰዎች ነበሩ፥ እኔን ለማመስገን የተመለሰ ግን አንድ ሰው ብቻ ነው” ሲል ተገረመ።
The Grateful Man
Luke 17:11-19
One time as Jesus was traveling towards Jerusalem, 10 men with a terrible skin disease saw him from some distance. They were not allowed to live among other people because of their disease. These men shouted, “Jesus, please heal us!” And Jesus responded, “Go to the priest so he can confirm your healing!” He said this because he knew that they would be healed before they got to the priest. The 10 men went just like Jesus had told them and were healed on the way. Then they showed the priest that they were healed from their skin disease. At that time, this was the normal way to confirm that you were healed.
However, only one of the 10 men returned to Jesus and thanked him from his heart. He was not even an Israelite. Jesus said to him “Go home in peace! Your faith in me has healed you.” In addition he said in wonder, “Did I not heal 10 men? But only one of them returned to thank me.”

ከተፈወሱት አሥር ሰዎች አንዱ ብቻ ተመልሶ ኢየሱስን ሲያመሰግን
ኢየሱስ ስንት ሰዎችን ፈወሰ?
ኢየሱስ አሥር ሰዎችን ፈወሰ።
ከተፈወሱት ውስጥ ስንት ሰዎች ኢየሱስን አመሰገኑ?
አንድ ሰው ብቻ ኢየሱስን አመሰገነ።
113. ሳያቋርጡ ስለ መጸለይ
ሉቃስ 18፥1-8
ሁልጊዜ ስለ መፀልይ ኢየሱስ እንዲህ ሲል አስተማረ፡-
ችግር ያጋጠማት አንዲት ሴት ነበረች። ወደ አንድ ዳኛ ሄዳ ከሰው ጋር በገጠማት ክርክር ትክክለኛውን ፍርድ እንዲፈርድላት ጠየቀችው። ዳኛው ግን እግዚአብሔርን የማይፈራ እና ሰውንም የማያከብር ስለነበር፥ ሊፈርድላት አልፈለገም። ይሁን እንጂ ሴትየዋ ተስፋ ሳትቆርጥ በተደጋጋሚ እየሄደች ትጠይቀው ነበር። በመጨረሻም ዳኛው ብዙ ጊዜ በጥያቄዋ ስላስቸገረችው፥ በትክክል ፈረደላት።
ኢየሱስም “ይህ ክፉ ዳኛ ለሴትየዋ ከፈረደላት፥ የሚወዳችሁ እግዚአብሔር ሳታቋርጡ ብትለምኑት በእርግጥ ይረዳችኋል” አለ።
Praying with Perseverance
Luke 18:1-8
Jesus taught about enduring prayer with this story:
There was a widow who was in trouble. So she went to a judge and asked him to give her fair judgement in the case that someone had raised against her. But the judge didn’t fear God, nor did he respect people and therefore he didn’t want to help her. However, the woman didn’t give up. She asked him again and again. Finally, the judge helped her by judging fairly since she bothered him so often.
Then Jesus said: “God cares so much more for you than the unrighteous judge cared about the woman. If you cry to him without giving up he will surely help you.”

አንዲት ሴት በችግሯ እንዲረዳት ክፉውን ዳኛ ስትለምን
እግዚአብሔር ሳንቋርጥ ብንለምነው ምን ያደርግልናል?
እግዚአብሔር ይረዳናል።
114. እግዚአብሔር የሚወደው ጸሎት
ሉቃስ 18፥9-14
ሁለት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ። አንደኛው ወደ ሰማይ እንኳን ቀና ብሎ ለማየት እየፈራ፡ “እባክህ እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ ጥፋተኛ ነኝና ይቅር በለኝ” ብሎ ጸለየ። ሌላው ትዕቢተኛ ሰው ስለነበረ “እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔ እንደዚህ ኃጢአተኛ ወይም እንደ ሌሎች ክፉ ሰዎች ስላልሆንኩ፥ አመሰግንሃለሁ። በሳምንት ሁለት ቀን እጾማለሁ፥ ገንዘብ ለቤትህ ስራ እሰጣለሁ” ብሎ ጸለየ።
እግዚአብሔር በትህትና “እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ይቅር በለኝ” ብሎ በጸለየው ሰው ተደሰተ። ራሱን ከፍ ከፍ ባደረገው ትዕቢተኛ ሰው ጸሎት ግን አልተደሰተም።
God-Pleasing Prayer
Luke 18:9-14
Two men prayed to God. The first one hardly dared to look up while he prayed. He said, “My God, I have done wrong. Please have mercy on me, forgive me!” But the other man was proud. He prayed, “My God, I want to thank you that I am not like this sinner or some other evil person. I fast two days a week and I give money towards the work in your house.”
God was pleased with the man who had prayed humbly, “I am a sinner, forgive me!” But he disliked the prayer of the proud man who trusted in his own goodness.

ትሑቱ እና ትዕቢተኛው ሰው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ
በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ሆነን መጸለይ አለብን?
ራሳችንን ዝቅ አድርገን በትሕትና መጸለይ አለብን።
115. ኢየሱስ ሕፃናትን ባረከ
ማርቆስ 10፥13-16 + ሉቃስ 18፥15-17
ሰዎች ሕፃናትን እንዲባርካቸው ወደ ኢየሱስ ይዘው መጡ። የኢየሱስ ተከታዮች ይህንን አይተው እንዳያስችግሩት ከለከሏቸው። ኢየሱስ ግን
“ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፥ አትከልክሏቸው” ብሎ ተቆጣቸው። ከዚህም በኋላ ሕፃናቱን አቅፎ ባረካቸው። በተጨማሪም “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ሕፃናት ለሆኑ ናት። ደግሞም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት እንደ ሕፃናት የምታምኑ መሆን አለባችሁ” አላቸው።
Jesus Blesses Children
Mark 10:13-16 + Luke 18:15-17
Some people brought their small children to Jesus. When Jesus’ followers saw this, they stopped them so that they would not bother him. But Jesus got angry and said, “Let the children come to me, don’t hinder them!” After this he embraced the children and blessed them.
Additionally Jesus said, “God’s Kingdom is for people who are like children. And you must trust God like a child does, in order to enter his Kingdom.”

ኢየሱስ ሕፃናትን ተቀብሎ አቅፎ ሲባርክ
እንደ እነማን በእግዚአብሔር መታመን አለብን?
እንደ ሕፃናት በእግዚአብሔር መታመን አለብን።
ምን ይመስላችኋል፥ ኢየሱስ እናንተንም በፍቅር ተቀብሎ ይባረካችኋል?
116. የይቅርታ አስፈላጊነት
ማቴዎስ 18፥21-35
እግዚአብሔር እኛን ሁልጊዜ ይቅር እንደሚለን፥ እኛም ያሳዘኑንን ሰዎች ይቅር ማለት አለብን። ኢየሱስም ስለዚህ ጉዳይ አንድ ታሪክ በመናገር አስተማረ፦
ከአንድ ንጉሥ በጣም ብዙ ዕዳ የተበደረ አንድ ሰራተኛ ነበር። የተበደረውን ገንዘብ ግን በጊዜ መመለስ አልቻለም። ንጉሡም ለተበዳሪው ሰው የነበረበትን ዕዳ በሙሉ በመተው ምሕረት አደረገለት። ይህም ምሕረት የተደረገለት ተበዳሪ ለሌላ ሰው ትንሽ ብድር ሰጥቶ ነበር። እርሱም ገንዘቡን በጊዜ ሊመልስለት አልቻለም። የንጉሡ ሰራተኛ ግን ተበዳሪውን ሊምረው አልፈለገም። ስለዚህ ወደ እስር ቤት አስገባው። ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጥቶ ክፉውን ሰራተኛ አስጠራው። እርሱን እንደማረው ሌላውን ሰው ለምን እንዳልማረ ጠየቀው። ብዙ ምሕረት አገኝቶ እርሱ ግን ምሕረት ስላላደረገ፥ ንጉሡ በጣም ቀጣው።
እኛም ለሌሎች ምሕረት ካላደረግን፥ እግዚአብሔር እኛንም አይምረንም።
The Importance of Forgiving
Matthew 18:21-35
Just like God forgives us constantly, we are to forgive our brothers and sisters in the same way. Jesus told a powerful story to teach on this topic:
There was a servant who had taken a huge loan from his king. But he was not able to pay it back in time. The king then decided to have mercy on him and cancelled his debt. This same servant had given a small loan to yet another man. And that man was also not able to pay back in time. But the king’s servant did not want to have mercy on the man and had him put in prison.
When the king heard about this, he got angry with the evil servant and had him come. He then asked him why he didn’t have mercy on the other man, even though he had received so much mercy himself. The king punished the evil servant since he had received so much mercy, yet was not merciful to others.
If we are not merciful to others, God will also not have mercy on us.

ምሕረትን የተቀበለው ሰራተኛ ለሌላ ሰው ምሕረት አላደርግም ሲል
ሰዎች ቢያሳዝኑን፥ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ ይፈልጋል?
ሁል ጊዜ ይቅርታ እንድናደርግላቸው ይፈልጋል።
117. የሀብታሙ ሰው ጥያቄ
ማቴዎስ 19፥16-26
አንድ ቀን አንድ ሀብታም ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ “የዘለአለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አክብር። ‘ሰውን አትግደል! ለሚስትህ ታማኝ ሁን! አትስረቅ! በውሽት በሰው ላይ አትመስክር! አባትህን እና እናትህን አክብር! ሰውን እንደራስህ ውደድ!’ የሚለውን ሕግ አድርግ” አለው። ሀብታሙም ሰው “ያልከውን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሁሉ አድርጌያለሁ” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም “አንድ ነገር ይቀርሀል። ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ! ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከታዬ ሁን” ብሎ ነገረው። ሀብታሙ ሰው ግን ብዙ ገንዘብ ስለነበረው፥ ይህንን ማደርግ በጣም ከበደው። ስለዚህ አዝኖ ኢየሱስን ትቶ ሄደ።
The Rich Man’s Question
Matthew 19:16-26
One day a rich man came to Jesus and asked him, “What do I have to do in order to receive eternal life?” Jesus answered, “Obey the commandments of God: Do not kill anyone. Obey the laws about marriage. Do not steal. When you speak as a witness, don’t lie. Honour your father and mother. Love your neighbour like you love yourself.” The rich man responded, “I have obeyed all God’s commandments you just mentioned.” Then Jesus told him, “What you still need to do is sell everything you own and give it to the poor. After that come and follow me!” But this was very hard for the man because he was really wealthy. So he became sad and went away.

ሀብታሙ ሰው ኢየሱስን የዘለአለም ሕይወት እንዴት ማግኘት እንደሚችል ሲጠይቀው
ሀብታሙ ሰው ኢየሱስን መከተል ያቃተው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔርን እና ሰዎችን ከመውደድ ይልቅ የራሱን ሀብት ስለወደደ ነው።
118. ኢየሱስ ዐይነ ስውሩን ፈወሰ
ሉቃስ 18፥35-43
አንድ ቀን ኢየሱስ በኢያሪኮ አካባቢ ከብዙ ሕዝብ ጋር ያልፍ ነበር። እዚያም አንድ ዐይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ገንዘብ ይለምን ነበር። ሰውየው ብዙ ጫጫታ ሲሰማ “ምን እየሆነ ነው?” ሲል ሰዎችን ጠየቀ። ሰዎቹም “ኢየሱስ እያለፈ ነው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ዐይነ ስውሩ “ኢየሱስ፥ ኢየሱስ! ማረኝ፥ እርዳኝ” ብሎ መጮኽ ጀመረ። አንዳንድ ሰዎች ዝም እንዲል ቢከለክሉትም፥ እርሱ ግን ይበልጥ ጮኸ። ኢየሱስም ሰምቶት ቆመ እና “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ዐይነ ስውሩም “ማየት እፈልጋለሁ” አለው። ስለዚህ ኢየሱስ
“እይ” ሲለው፥ ወዲያው ማየት ቻለ። እግዚአብሔርን ከልብ አመስግኖ ኢየሱስን ተከተሎ ሄደ።
Jesus Heals a Blind Man
Luke 18:35-43
One day Jesus was walking with a big crowd near the city of Jericho. There a blind man was sitting beside the road begging for money. When the man heard a lot of noise, he asked, “What is happening?” People explained to him that Jesus was passing by. So the blind man started to call “Jesus, have mercy on me, help me!” When some people told him to be quiet, he shouted even louder. Jesus heard him, stopped and asked him “What is it that you want me to do for you?” The blind man answered, “I want to see!” And Jesus healed him. Immediately he was able to see. He praised God wholeheartedly and went with Jesus.

ኢየሱስ ዐይነ ስውር ሲፈወስ
ዐይነ ስውሩ ኢየሱስን ምን እንዲያደርግለት ለመነው?-
ኢየሱስ ዐይኑን እንዲፈወሰለት ለመነው።
119. ኢየሱስ ሁሉንም ሰው ይወዳል
ዮሐንስ 4፥1-42
እስራኤላውያን የሰማርያን ሕዝብ አይወዷቸውም ነበር። ኢየሱስ ግን እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆን፥ ሳምራውያንንም ይወዳል። አንድ ቀን ከተከታዮቹ ጋር በሰማሪያ በኩል ሄደ። በዚያም በአንዲት ከተማ ሲያልፍ ውሃ ለመቅዳት የመጣች ሴትን አነጋገረ። በሕይወትዋም ዘመን ያደረገችውን ነገር እስክትደነቅ ድረስ ነገራት። ኢየሱስም እርሱ የሕይወትን ውሃ የሚሰጥ መሆኑን አሳወቃት። ይህም ውሃ ኢየሱስን በማመን የሚገኝ የዘለአለም ሕይወት ነው። እርሱም ልብን በሰላም ይሞላል። ከዚህ በኋላ ሴትየዋ ወደ ከተማ ሄዳ ለሕዝቡ ኢየሱስ ሚስጥሯን ሁሉ እንዳወቀ ነገረቻቸው። ንግግርዋንም ሰምተው ብዙ የሰማሪያ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ። ከእነርሱም ጋር እንዲቆይ ስለለመኑት፥ ለሁለት ቀናት አብሯቸው ሆነ። ብዙ የሰማሪያ ሰዎችም ኢየሱስ እግዚአብሔር የላከው አዳኝ እንደሆነ አመኑ።
Jesus Loves All People
John 4:1-42
Israelites didn’t like people from Samaria. Jesus, however, does not only care about Israelites but also about Samaritans. One day he travelled through the land of Samaria with his disciples. Outside one of the towns Jesus started a conversation with a woman who had come to draw water at the well. He prophetically told her things she had done in the past. The woman was amazed that he knew all these things. Jesus also made clear to her that he is the one who gives living water. This water is the eternal life that someone receives, when he believes in Jesus. And it also fills people’s hearts with peace.
After this conversation, the woman went into town and told the people that Jesus supernaturally knew everything about her. On hearing this, many Samarians came and listened to Jesus. When they begged him to stay with them, he agreed and was their guest for two days. Many people there believed that Jesus is the Saviour whom God had sent.

ኢየሱስ ከሳምራዊትዋ ሴት ጋር ሲነጋገር
ኢየሱስ የሕይወት ውሃ እሰጣለሁ ሲል ምን ማለቱ ነው?
ይህ የሕይወት ውሃ ኢየሱስን በማመን የሚገኝ የዘለአለም ሕይወት መሆኑን ነው።
ኢየሱስ ማንን ይወዳል?
የእስራኤልን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፥ ሰዎችን ሁሉ ይወዳል።
120. ኢየሱስ እና ዘኬዎስ
ሉቃስ 19፥1-10
ገንዘብ ከሚገባው በላይ ከሕዝብ በመውሰድ ሀብታም የሆነ ዘኬዎስ የሚባል ሰው ነበር። አንድ ቀን ኢየሱስ በሚኖርበት ከተማ እንደሚያልፍ ሰማ። እርሱም ኢየሱስን በጣም ማየት ፈለጎ ነበር። ቁመቱ ግን አጭር ስለነበር፥ ለማየት እንዲችል ዛፍ ላይ ወጣ። ኢየሱስም ቀና ብሎ ወደላይ አይቶት “ዘኬዎስ፥ ና ውረድ! ዛሬ በቤትህ መዋል እፈልጋለሁ” አለው። ዘኬዎስም በደስታ ከዛፉ ወርዶ ወደ ቤቱ ጋበዘው። እርሱም ኢየሱስን “ከሀብቴ ግማሹን ለድሆች እሰጣለሁ። ከሰውም ከመጠን በላይ የወሰድኩትን አራት እጥፍ እመልሳለሁ” ብሎ ተናገረ። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ለዘኬዎስ “ዛሬ ከጥፋት መዳን ሆነልህ” አለው።
ከዚህ ታሪክ የምንማረው፥ ኃጢአታቸውን ትተው ወደ እግዚአብሔር ለተመለሱ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ምሕረትን እንደሚያደርግ ነው።
Jesus and Zacchaeus
Luke 19:1-10
There was a man named Zacchaeus. He was rich, because he took more money from people than he was supposed to. One day he heard that Jesus was passing through his town. He really wanted to see Jesus, but because he was a short man, he had to climb a tree in order to see him. When Jesus got there, he looked up and said to him, “Come down, Zacchaeus. I want to be your guest today.” Full of joy Zacchaeus came down and welcomed him into his house.
There he told Jesus, “I will give half of my possessions to the poor. And when I have taken too much from someone, I will give him back four times as much.” At this Jesus responded to Zacchaeus “You received salvation today.”
What we can learn from this story is that Jesus has mercy on anyone who stops doing evil things and turns to God.

ዘኬዎስ ዛፍ ላይ ወጥቶ ኢየሱስን ሲያይ እና ኢየሱስ ሲጠራው
ዘኬዎስ ጥፋቱን ካወቀ በኋላ፥ ምን አደረገ?
ከሰዎች ከሚገባው በላይ የወሰደውን ገንዘብ ሲመለሰ፥ ከሀብቱ ግማሹን ለድሆች ሰጠ።
121. ኢየሱስ በአህያ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም ገባ
ሉቃስ 19፥28-44
ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ከመድረሱ በፊት ከተከታዮቹ ሁለቱን ወደ ቅርብ መንደር ሄደው አንድ አህያ እንዲያመጡለት ነገራቸው። ከዚህ በፊት በአህያው ላይ ማንም ተቀምጦ አያውቅም ነበር። ተከታዮቹ አህያውን ካመጡለት በኋላ፥ ኢየሱስ ተቀምጦበት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። በዚህ ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ። ኢየሱስ ስላደረገውም ድንቅ ነገሮች ሁሉ በደስታ ተሞልተው በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እነርሱም “በእግዚአብሔር ስም ለሚመጣው ንጉሥ ክብር እና ምስጋና ይሁን!” ብለው ጮኹ።
ይህ የሆነው ኢየሱስ ከመሞቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ነው። በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ሰዎች ግን እርሱ አዳኝ እና የሰላም ንጉሥ መሆኑን አላወቁም ነበር። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ስለሚመጣባቸው መከራ አውቆ አለቀሰላቸው።
Jesus Enters Jerusalem on a Donkey
Luke 19:28-40
Before arriving in Jerusalem, Jesus sent two of his followers ahead to a nearby village. He told them to bring a certain donkey from there. Nobody had ever sat on it before. Jesus then rode on that donkey into Jerusalem, whilst the people who were with him rejoiced greatly. They praised God loudly for all the amazing things Jesus had done. In addition, they put their clothes on the road in front of him. And they shouted “Honour and praise to the king who comes in God’s name!”
This happened about one week before Jesus died. But at that time, the people of Jerusalem didn’t realise that he was the Saviour and the King of Peace. So Jesus cried since he knew how much suffering would come upon them.

ኢየሱስ በአህያ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲገባ
ኢየሱስ እንደ ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፥ ከእርሱ ጋር የመጡት ምን አደረጉ?
ሕዝቡ በከፍተኛ ድምፅ እየጮሁ እና ልብሳቸውን በመንገድ ላይ እያነጠፉ ኢየሱስን እና እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
122. የእግዚአብሔር ቤት የንግድ ቦታ አይደለም
ዮሐንስ 2፥13-23 + ማርቆስ 11፥15-19 + ሉቃስ 19፥45-48
ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ፥ ሰዎች ቅዱሱን ቦታ የንግድ ቤት አድርገውት አየ። የጸሎት ቤት መሆን የነበረበትን የገበያ ሰፍራ ስላደረጉት ተቆጣ። ስለዚህም እንስሳቱን፥ ነጋዴዎቹን እና ደንበኞቻቸውን ከቤተ መቅደሱ አባረራቸው። ከዚያ በኋላ በቤተ መቅደስ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተማረ። ተአምራትንም ስላደረገ፥ ብዙዎች በእርሱ አመኑ። አብዘኛው የእስራኤል መሪዎች ኢየሱስ ባደረገው ነገር ተቆጥተው ሊገድሉት ፈልገው ነበር። ሕዝቡ ግን ኢየሱስን ወደውት ስለነበር፥ በቀላሉ ይህንን ማድረግ አልቻሉም።
God’s House Is Not a Market
Mark 11:15-19 + John 2:13-23
When Jesus came to the Temple in Jerusalem, he saw that this holy place had been turned into a marketplace. It should have been used as a house of prayer though! So, Jesus got angry. He chased all the animals, businesspeople and their customers out of God’s house. Later that day, Jesus taught the people in the temple about the Kingdom of God and did miracles. Many people believed in him. It was mainly the leaders of Israel who were angry about the things Jesus did and therefore wanted to kill him. But it was not easy for them to do so since the crowd liked him.

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚደረገውን ገበያ ሲያስቆም
ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቤት የንግድ ቤት መሆኑን ሲያይ ለምን ተቆጣ?
ቤተ መቅደሱ የጸሎት ቤት ብቻ መሆን ስለነበረበት ተቆጣ።
123. እኩል ደመወዝ ያገኙ ሰራተኞች
ማቴዎስ 20፥1-16
ትልቅ የወይን እርሻ የነበረው አንድ ሰው ነበር። የእርሻውን ፍሬ እንዲሰበስቡለት ሰራተኞች ፍለጋ በማለዳ ወደ ገበያ ሄደ። በገበያውም ሰራተኞችን አግኝቶ በደመወዝ ከተስማሙ በኋላ ቀጠራቸው። ከተወሰነ ሰዓት በኋላ እንደገና ሄዶ ተጨማሪ ሰራተኞችን ቀጠረ። ከሰአት በኋላም እንደገና ስራ ያላገኙ ሠራተኞችን አግኝቶ ቀጠራቸው።
በመሸም ጊዜ ደመወዝ ሲከፈል፥ ለሁሉም እኩል ከፈላቸው። በዚህም መጨረሻ ላይ ለመጡት ሰራተኞች መልካም አደረገላቸው። በማለዳ ተቀጥረው የሰሩት ሰራተኞች ግን በኋላ ከመጡት እኩል ስለተከፈላቸው፥ ቅሬታ አቀረቡ። የወይን እርሻ ባለቤትም “እኔ የተስማማነውን ደመወዝ ሰጠኋችሁ እንጂ፥ አልቀነስኩባችሁም። ከኋላ ለመጡት ሰዎች መልካም ስላደረግሁላቸው ለምን ትቀናላችሁ?” አላቸው።
The Same Wages for All
Matthew 20:1-16
Jesus told another story to teach:
There was a man who had a big field with plants called grape vines. At harvest time he needed many workers to collect all the fruit. And so early in the morning, he went into town and found some workers there. He agreed with them on their pay and hired them. Later in the day, he went again and hired additional workers. And when he saw some workers in the afternoon who had not found work, he hired them too.
In the evening he paid the same wages to all the workers. This way he did good to those who had come late. However, the workers who had started early in the morning complained because they had worked much longer. Then the landowner answered, “I didn’t cut your wages! I definitely gave you what we agreed upon. I just chose to be generous to those who started work later. So why are you jealous?”

ብዙ እና ትንሽ ሰዓት የሰሩ ሰራተኞች ሁሉ እኩል ደመወዝ ሲያገኙ
የወይን እርሻው ባለቤት በተለያየ ሰዓት ለቀጠራቸው ሰራተኞቹ ምን አደረገ?
ለሁሉም እኩል ደመወዝ ከፈላቸው።
መልካም ያደረገው የእርሻው ባለቤት የማንን ባህሪ ይመስላል?
የእግዚአብሔርን ባህሪ ይመስላል።
124. ለመንግሥት እና ለእግዚአብሔር መስጠት
ሉቃስ 20፥20-26
ኢየሱስ በእስራኤል መሪዎች ላይ በምሳሌ ስለ መጥፎ ስራቸው ስለተናገረ ተናደዱበት። ሊያስሩትም ፈልገው ሕዝቡን ስለፈሩ አልቻሉም። ስለዚህ እርሱን ለማሳሳት በተንኮል “ለሮም መንግሥት ገንዘብ መክፈል ይፈቀዳል?” በማለት ጠየቁት። እርሱ ግን “አንድ ሳንቲም አሳዩኝ” አላቸው። ሲያሳዩትም “በዚህ ሳንቲም ላይ ያለው ምስል የማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “የታላቁ የሮም ንጉሥ ነው” ብለው መለሱለት። ከዚያም ኢየሱስ የንጉስ የሆነውን ለንጉሡ እንዲሰጡ ደግሞም የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር መስጠት እንዳለባቸው ነገራቸው። ሰዎቹም ጥበብ በተሞላው መልሱ ተገረሙ።
Giving to God and to the Government
Luke 20:20-26
The leaders of Israel were upset with Jesus because he pointed out their evil deeds by telling stories. As a result, they wanted to arrest him, but they were not able to since they were afraid of the crowd. They wanted to mislead him and therefore asked him this tricky question, “Are we allowed to pay taxes to the great King of Rome?” Jesus responded, “Show me a coin,” and when they showed it, he asked “Whose picture is on this coin?” They answered “It is the picture of the great King of Rome.” Jesus then told them that they should give to the king what belongs to the king. And they should give to God what belongs to God. The leaders were amazed by his wise answer.

ኢየሱስ ለተንኮለኛ ጥያቄዎች በጥበብ መልስ ሲሰጥ
መሪዎቹ ኢየሱስን በተንኮለኛ ጥያቄያቸው ማሳሳት ቻሉ?
አይ፥ ሊያሳሰቱት አልቻሉም።
125. አልዓዛር ከሞት ተነሳ
ዮሐንስ 11፥1-44
አልዓዛር፥ ማርታ እና ማርያም ኢየሱስ የሚወዳቸው ቤተሰብ ነበሩ። አንድ ቀን አልዓዛር በጣም ታመመ። ኢየሱስም መታመሙን ቢሰማም፥ ወደ እርሱ ሳይሄድ ባለበት ቦታ ሁለት ቀን ቆየ። አልዓዛርም በጣም ስለታመመ፥ በመጨረሻ ሞቶ ተቀበረ። ኢየሱስ የሚወደው በታመመ ሰአት ያልሄደበት ምክንያት፥ አልዓዛርን ከሞት በማስነሳት ሕዝቡ በእርሱ እንዲያምኑ ነበር።
እርሱም አልዓዛር ከሞተ ከአራት ቀን በኋላ ወደ ልቅሶው አካባቢ ቀረበ። እነ ማርታም መምጣቱን ሲሰሙ ሄደው አገኙት። ከዚያም ከማርታ፥ ከማርያም እና ከአጽናኞችዋ ጋር አልዓዛር ወደ ተቀበረበት ሰፍራ ሄደ። እዚያም ፀሎቱን ሁልጊዜ ስለሚሰማው እግዚአብሔርን አመስግኖ “አልዓዛር፥ ና፥ ውጣ!” ብሎ ጠራው። ወዲያውኑ ከሞት ተነስቶ ከመቃብር ወጣ። ሕዝቡም ይህንን ባዩ ጊዜ በጣም ተገረሙ። ብዙዎችም ኢየሱስ እግዚአብሔር የላከው አዳኝ መሆኑን አውቀው በእርሱ አመኑ።
Lazarus Rises from Death
John 11:1-44
Lazarus, Martha and Mary were friends of Jesus. One day Lazarus became very sick. When Jesus heard about this, he stayed where he was for two more days. Since Lazarus was very sick, he finally died. The reason why Jesus didn’t go to him immediately was that he wanted to raise him from death, so that the people would believe in him.
Lazarus had already been dead for four days when Jesus finally came to Lazarus’ village. When Martha and Mary heard that Jesus was near, they each went to meet him. Afterwards, Jesus went to the grave together with them and their mourning friends. There he thanked God that he always hears his prayer. Then he called, “Lazarus, come out!” And immediately Lazarus rose from death and came out of the grave. The people were astonished when they saw what happened and many believed that Jesus is the Saviour.

ኢየሱስ የሞተውን አልዓዛር ከመቃብር እንዲወጣ ሲጠራው
ኢየሱስ አልዓዛር በታመመ ሰአት ያልመጣው ለምንድን ነው?
ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት በማስነሳት እግዚአብሔር የላከው አዳኝ እንደሆነ እንዲያምኑ ነው።
126. ያላትን ትንሽ ገንዘብ የሰጠችው ሴት
ሉቃስ 21፥1-4
አንድ ቀን ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ ገባ። በዚያም ሰዎች ለእግዚአብሔር ስጦታ ሲሰጡ ተመለከተ። አንዳንድ ሀብታም ሰዎችም ብዙ ገንዘብ ሲሰጡ አየ። አንዲት ድሀ ሴት ግን ያላትን ትንሽ ሳንቲም ሰጠች። ኢየሱስም ለተከታዮቹ ድሀዋ ሴት ከሀብታሞች ይበልጥ እንደሰጠች ነገራቸው። ምክንያቱም እርሷ ያላት ሁለት ሳንቲም ቢሆንም፥ ሁሉንም ስለሰጠች ነበር። ሀብታሞቹ ግን የሰጡት ካላቸው ገንዘብ ጥቂቱን ብቻ ነው።
The Poor Woman Gives Much
Luke 21:1-4
One day Jesus went to the Temple with his followers. There he observed people giving gifts to God. He noticed that some rich people gave a lot of money. But he also saw how a poor widow gave only two small coins. After this, Jesus explained to his disciples that the poor woman had given more than the rich people because she had given all that she had. The rich people, however, had only given a small part of their wealth.

ሰዎች ለእግዚአብሔር ገንዘብ ሲሰጡ እና ኢየሱስ ሲመለከት
ትንሽ ሳንቲም መስጠት እንዴት ብዙ ሊሆን ይችላል?
ያለን ገንዘብ ትንሽ ቢሆን እንኳን፥ ሁሉንም ከሰጠን ብዙ ነው።
127. በተሰጠን መስራት
ማቴዎስ 25፥14-30
አንድ ሀብታም ሰው ሠራተኞቹን ጠርቶ ነግደው እንዲያተርፉበት ለእያንዳንዳቸው ገንዘብ ሰጣቸው። ከዚያም ወደ ሌላ ሩቅ ሀገር ሄደ።
ሀብታሙ ሰው ከተመለሰ በኋላ ሠራተኞቹን እንደገና ጠራ። ሁለቱ ሰዎች በተሰጣቸው ገንዘብ በጥሩ ሁኔታ ሰሩበት። ስለዚህ ከተሰጣቸው በላይ ብዙ ትርፍ አገኙ። በዚህ ምክንያት ባለሀብቱ ሸለማቸው። ሦስተኛው ሰው ግን በተሰጠው ገንዘብ ስላልሰራበት፥ ምንም አላተረፈም። ስለዚህ ባለሀብቱ ሰነፉን ሰው ተቆጥቶ የሰጠውን ገንዘብ ወሰደበት።
ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን በጥሩ ሁኔታ ከተጠቀምንበት እየበዛ ይሄዳል።
Using What We Received
Matthew 25:14-30
There was a rich man who called his workers and told them to trade and make profit with his money. Then he went on a long journey.
After he returned, he called his workers again. Two of them did very well. They had made a lot of profit on top of what they were given. Therefore, their wealthy master rewarded them well.
But the third man didn’t do anything with the money he was given. And, therefore, he didn’t gain anything. As a result the master got angry at the lazy man and took away the money he had given in his care.
What we have received from God will grow, when we use it well.

ባለሀብቱ የተቀበለውን ገንዘብ ስላልሰራበት በሰነፉ ሰው ላይ ሲናደድ
ሦስተኛው ሰው የተቀበለው ገንዘብ ለምን ተወሰደበት?
እንዲነግድበት የተሰጠውን ገንዘብ ምንም ስላልሰራበት ነው።


በታሪክ 104-127 ፈልግ፡