Oromo 1 – 25
Addaam – Yooseef,
Adam – Joseph


ታሪኮችን ለመክፈት ከዚህ በታች የምትፈልጉትን ተጫኑ
WORK in PROGRESS
1. Seera uumamaa
Seera Uumamaa 1
Jalqabarratti, Waaqayyo samii fi lafa uume. Yeroo sanatti dukkana qofatu ture. Hangayeroo sanaatti wanti gaarii ta’ee fi tartiiba qabate hin turre , Kanaaf Waaqayyo dubbiitokko dubbachuudhaan waan hundumaa gaarii fi sirna qabeessa taasise. Waaqayyoaduu, ji’aa fi urjii uume. Haala kanaan halkanii fi guyyaa hojjete.
Creation: 
Genesis 1
In the beginning God created heaven and earth. The world was dark at that time and there was nothing orderly or beautiful yet. Therefore God created a good order and made everything beautiful.
God created sun, moon and stars and in this way he separated day from night.

ዓለም በመጀመሪያ በሥርዓት የተቀመጠች አልነበረችም።
Lafaa fi samii eenyutu uume? 
Lafaa fi samii Waaqayyotu uume.
2. not ready 
ዘፍጥረት 1-2
እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ወንዞችን እና ሐይቆችን ፈጠረ። በተጨማሪም ተራራዎችን፥ ዛፎችን፥ ተክሎችን እና ብዙ ዐይነት እንስሳትን ፈጠረ። የፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ በጣም ቆንጆ እና ያማሩ ሆኑ። ምድርንም በጣም ጥሩ ቦታ አደረገ። እግዚአብሔርም በሰራው ስራ ተደሰተ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ዐፈር ወስዶ ሰውን ፈጠረ። ስሙም አዳም ይባል ነበር። አዳምም ብቻውን እንዳይሆን ከባድ እንቅልፍ ሲተኛ እግዚአብሔር ከጎኑ አጥንትን ወስዶ ሴትን ፈጠረ። እርሷም ለአዳም ሚስት ሆነችው። አዳምም ሔዋን ብሎ ስም አወጣላት። እግዚአብሔር ገነት በምትባል በጣም በሚያምር የተክሎች ስፍራ አስቀመጣቸው።
God Creates Everything Beautifully 
Genesis 1-2
God created heaven, the earth, rivers and lakes. Additionally he created mountains, birds, plants and many different animals. Everything became very beautiful. Now the earth was a wonderful place. And God was pleased by all that he had made.
Some time later God took soil and created a man. The man was called Adam. In order for Adam not to be alone, God took a rib from his side while he was fast asleep and created a woman to be his wife.
Adam gave her the name Eve. And God put both of them in a very beautiful garden – in paradise.

አዳም እና ሌሎች ፍጥረታት
እግዚአብሔር የመጀመሪያዎቹን ሰዎች ያስቀመጣቸው በምን ዐይነት ቦታ ነበር? 
ገነት በምትባል በምታምር የተክሎች ስፍራ አስቀመጣቸው።
3. not ready
ዘፍጥረት 3
አዳም እና ሔዋን በዚህ አስደናቂ ስፍራ ውስጥ መኖር ጀመሩ። እግዚአብሔርም ወደ እነርሱ ቀረበ። እዚያም የሚገኙትን ብዙ የፍራፍሬ ዐይነቶች በመብላት እንዲደሰቱ ፈቀደላቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር ከአንዲት የዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ ከለከላቸው። ይህችን ፍሬ ከበሉ ግን ከእርሱ ተለይተው እንደሚሞቱ አስጠነቀቃቸው።
አንድ ቀን ሰይጣን እባብ በመምሰል ወደ ሔዋን መጥቶ “ከተከለከላችሁት ፍሬ ብትበሉ ምንም አትሆኑም” አላት። ከዚያም “እግዚአብሔርን መታዘዝ አያስፈልግም” በማለት በውሸት አሳመናት። በተጨማሪም “ፍሬዋን ከበላችሁ በኋላ እንደ እግዚአብሔር መልካም እና ክፉ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ” በማለት አታለላት። ስለዚህም ሔዋን ከዛፏ ፍሬ በላች። ለአዳምም ሰጠችው፥ እርሱም በላ።
The Forbidden Fruit
Genesis 3
Adam and Eve started to live in this wonderful place. And God was close to them there. He allowed them to enjoy the many fruits of the garden. Only from one tree they were not permitted to eat. God warned them that they would have to die if they ate from its fruit. And they would be separated from him.
One day Satan came to Eve in the form of a snake and tricked her with a lie. He said to her, “Nothing bad will happen when you eat from the forbidden fruit. You do not need to obey God. When you eat this fruit you will know what is evil and what is good.” Eve believed him, ate from the fruit and gave it to Adam as well. And so he ate from it too.

አዳም እና ሔዋን ከተከለከለው ፍሬ ሲበሉ
አዳም እና ሔዋን የማንን ምክር ሰምተው አደረጉ?
በእባብ አምሳል የመጣውን የሰይጣንን ምክር ሰምተው አደረጉ።
4. not ready
ዘፍጥረት 3፥1-24
እግዚአብሔር አዳም እና ሔዋን ባደረጉት ነገር በጣም አዘነ። በዚህ ምክንያት ቀጣቸው። ቆንጆ ከሆነችውም ገነት አባረራቸው። እግዚአብሔርን ስላልታዘዙ፥ ከእርሱ ተለይተው አስቸጋሪ ኑሮ መኖር ጀመሩ። እግዚአብሔር ግን ስለሚወዳቸው በቅጣቱ አልተደሰተም። ስለዚህ ወደፊት መልካም ሕይወትን ለሰዎች እንደገና ሊመልስ አቀደ።
Adam and Eve Have to Leave
Genesis 3:1-24
God was very sad about what Adam and Eve had done. And he punished them. They had to leave the wonderful paradise and started a difficult life separated from God. But since he loved them he didn’t like to punish them. So he made a plan to restore the good life to the people in the future.

አዳም እና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ፥ ኑሮ አስቸጋሪ ሲሆንባቸው
አዳም እና ሔዋን ከገነት ለምን ተባረሩ?
እግዚአብሔርን ስላልታዘዙ ነው።
5. not ready
ዘፍጥረት 4
አዳም እና ሔዋን ልጆች ወለዱ። ስማቸውም ቃየን እና አቤል ተባለ። አቤል ለእግዚአብሔር ስጦታ ሰጠ። (መልካም ሰውም ስለነበር፥) እግዚአብሔርም ስጦታውን በደስታ ተቀበለ።
ወንድሙም ቃየን ለእግዚአብሔር ስጦታ ሰጠ። እግዚአብሔር ግን ስጦታውን አልተቀበለም፥ ምክንያቱም ቃየን ታዛዥ ልጅ አልነበረም።
እግዚአብሔር ስጦታውን ስላልተቀበለው፥ ቃየን በጣም ተናደደ። ቃየን እግዚአብሔር የሚለውን ቢሰማ ኖሮ፥ የእርሱንም ስጦታ ይቀበለው ነበር። እርሱ ግን እግዚአብሔርን አልሰማም። በመጨረሻም ወንድሙ አቤልን ገደለ። ቃየን ያደረገው ነገር በጣም መጥፎ ነበር። ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ቀጣው። ነገር ግን እግዚአብሔር የምሕረት አምላክ ስለሆነ፥ ማንም እንደማይገድለው ቃል ገባለት።
አዳም እና ሔዋን ተጨማሪ ሌሎች ልጆችን ወለዱ።
Cain and Abel
Genesis 4
Adam and Eve had children. Their names were Cain and Abel. Abel gave a gift to God. And God happily received his gift.
His brother Cain gave a gift to God as well. But God didn’t accept his gift since he did not have a good attitude.
Cain became very angry because God didn’t accept his gift. If Cain would have listened to God and lived accordingly, his gift too would have been accepted. But he didn’t listen to God. He ended up killing his brother. That was evil indeed. And God punished him for it. Yet because God is a God of mercy he promised him that nobody would kill him in revenge.
Adam and Eve had additional children after Cain and Abel.

ቃየን ስላልታዘዘ፥ ክፉ ስራ ሲሰራ
እግዚአብሔር የአቤልን ስጦታ የተቀበለው ለምንድን ነውu003cstrongu003e?u003c/strongu003e
አቤል ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ልጅ ስለነበር ነው።
6. not ready
ዘፍጥረት 7
ሰዎች በዓለም ላይ እየበዙ መሄድ ጀመሩ። ዓለምም በብዙ ክፉ አስተሳሰቦች እና በመጥፎ ስራዎች ተሞላች። እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ነገር በጣም አዘነ። እንደዚህ ዐይነት ብዙ መጥፎ ነገሮችን ከእንግዲህ ማየት አልፈለገም።
እግዚአብሔርም በሰዎች መካከል አንድ መልካም ሰው አገኘ። ያም ሰው ኖኅ ይባል ነበር። እግዚአብሔርም ኖኅን “ይህንን ዓለም እና ክፉ ሰዎችን በውሃ ስለማጠፋ፥ ለአንተ እና ለቤተስቦችህ መርከብ ስራ!” አለው። እግዚአብሔር ለኖኅ መርከቧን እንዴት መስራት እንዳለበት ነገረው። ኖኅ እግዚአብሔር እንዳለው መርከቧን ሰራ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከእያንዳንዱ የእንስሳት ዐይነት ወደ መርከቧ እንዲያስገባ አዘዘው። ደግሞም ለሁሉ የሚበሉትን ምግብ እንዲያስገባላቸው ተናገረው። ከዚያም በኋላ ኖኅ እና ቤተሰቡ እንሰሳቱም ወደ መርከቧ ውስጥ ገቡ። ወዲያውም የጥፋት ውሃ መጣ። እግዚአብሔር ግን ኖኅን እና ቤተሰቡን ከጥፋት አዳነ።
Noah
Genesis 7
As the number of people on the earth increased, it was filled with evil thoughts and deeds. God was really sad about this and did not want to see the evil things any longer.
But he saw that there was still one good person among the people. His name was Noah. And God said to him, “Build a ship for yourself and for your family, because I will destroy the world and its evil people by a flood!” He also told Noah how to build it. And Noah made it just as he was told. After that God told him to put animals of each kind and food for all of them into the ship. Then Noah, his family and the animals entered the ship. Immediately afterwards the earth started to flood. But God saved Noah and his family.

የተለያዩ እንስሳት ወደ መርከቧ ሲገቡ
እግዚአብሔር ለምን አዘነ?
የሰዎች መጥፎ ስራ በዓለም ላይ ስለበዛ ነበር።
እግዚአብሔር ኖኅን ከጥፋት ለማዳን ለምን ፈለገ?
ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ መልካም ሰው ስለነበር ነው።
7. not ready
ዘፍጥረት 8-9
የጥፋትም ውሃ ምድርን ለብዙ ወራት ሸፈነ። በዓለም ላይ የነበሩ ፍጥረታትን በሙሉ አጠፋቸው። ኖኅ እና ቤተሰቡ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩ እንስሳት ብቻ ከጥፋት ዳኑ።
ከመሬት ላይ ውሃው ከደረቀ በኋላ፥ ሁሉም ከመርከቧ ውስጥ ወጡ። ከዚህም በኋላ ኖኅ እግዚአብሔርን አመሰገነ።
እግዚአብሔርም ኖኅን እና ልጆቹን ባረካቸው። እንዲሁም በዓለም እንደገና እንዲባዙ ተናገራቸው። ሁለተኛ እንደዚህ ዐይነት የጥፋት ውሃ ልኮ ምድርን እንደማያጠፋም ቃል ኪዳን ገባላቸው። እግዚአብሔርም ለዚህ የቃል ኪዳን ምልክት እንዲሆን ቀስተ ደመናን በሰማይ ላይ አደረገ። አሁንም ይህን ምልክት አንዳንድ ጊዜ በሰማይ ላይ ይታያል።
God’s Promise to Noah
Genesis 8-9
The flood water covered the earth for many months. It destroyed all living creatures on earth. Only Noah, his family and the animals that were in the ship survived.
After the water had disappeared they all got out of the ship and Noah worshiped and thanked God.
And God blessed Noah and his children. He told them to multiply. He also promised that he would never again send such a terrible flood. As a sign of this promise he put a rainbow in the sky. Sometimes we can still see this sign.

ኖኅ እና ቤተሰቡ እግዚአብሔርን ሲያመልኩ
ቀስተ ደመና የምን ምልክት ነው?
አግዚአብሔር ሰዎችን ሁለተኛ በውሃ እንደማያጠፋ የሰጠው የቃል ኪዳን ምልክት ነው።
8. not ready
ዘፍጥረት 10-11
ከብዙ ዓመታት በኋላ ሰዎች በዓለም ላይ እንደገና እየበዙ ሄዱ። በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ አንድ ዐይነት ቋንቋ ይናገሩ ነበር። እነርሱም “ሁላችንም በዚህ አካባቢ እንኑር፥ ትልቅ ከተማ እና ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ” ተባባሉ። ይህ አስተሳሰባቸው ጥሩ ስላልነበረ፥ እግዚአብሔር አልወደደውም። ስለዚህ የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲናገሩ አደረጋቸው። ከዚህም የተነሳ እርስ በእርሳቸው መግባባት ስላልቻሉ፥ የጀመሩትን ስራ አቆሙ። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ በተናቸው።
The Story of Babylon
Genesis 10-11
Many years later there were many people on earth again. At that time they were all speaking the same language. They said to each other, “Let’s all live together in just one area! Let’s build a large city with a tower that reaches to the sky!” God was displeased because their thinking was not good. So he caused them speak many different languages. Then they didn’t understand each other any longer. Therefore they stopped the building work that they had started. This way God made the people spread out and live in different areas of the world.

ሰዎች የተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ከጀመሩ በኋላ፥ ግንቡን መስራት ሲያቆሙ
እግዚአብሔር ሰዎች የተለያዩ ቋንቋዎች እንዲናገሩ ካደረገ በኋላ ምን ሆነ?
የጀመሩትን ግንብ መስራት አቁመው በዓለም ተበተኑ።
9. not ready
ዘፍጥረት 12
አብራም በትውልድ ሀገሩ ከቤተስቦቹ ጋር ይኖር ነበር። አንድ ቀንም እግዚአብሔር “እባርክሃለሁ፥ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ እና እኔ ወደምልህ ወደ ሩቅ አገር ሂድ!” ብሎ ተናገረው። ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር እንዳለው ከሚስቱ ከሦራ እና ከአጎቱ ልጅ ከሎጥ ጋር ያለውን ንብረት ይዞ ሄደ። ከብዙ ጉዞ በኋላ ከነዓን በምትባል ሀገር ደረሱ። እግዚአብሔርም አብራምን “ይህንን ሀገር ለወደፊት ለዘርህ እሰጣለሁ” ብሎ የተስፋ ቃል ሰጠው።
God Calls Abram
Genesis 12
Abram lived with his family in his home country. But one day God said to him, “I will bless you, a large nation will come from you! Go to a faraway land that I will show you!” Abram therefore took his belongings and left together with his wife and his nephew Lot. After a long, long journey they arrived in a land called Canaan. And there God promised him, “In the future I will give this land to your offspring!”

አብራም የትውልድ ሀገሩን ትቶ ሲሄድ
አብራም የትውልድ ሀገሩን ለምን ትቶ ሄደ?
እግዚአብሔር ስለተናገረው ሀገሩን ትቶ ሄደ።
10. not ready
ዘፍጥረት 13
አብራም እና የወንድሙ ልጅ ሎጥ ብዙ እንስሳት ነበራቸው። ለእንስሳቶቻቸው ሁሉ ግን በቂ ምግብ አልነበረም። በዚህም ምክንያት እረኞቻቸው መጣላት ጀመሩ። ስለዚህ አብራም ሎጥን “እኛ ዘመዳሞች ስለሆንን፥ መጣላት እና መጨቃጨቅ የለብንም! የምትፈልግውን ቦታ መርጠህ በተለያዩ ቦታዎች እንኑር” ብሎ ምርጫ ሰጠው። ሎጥም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ለምለም እና አረንጓዴ ስፍራ መርጦ ሄደ። አጎቱ አብራም ግን በደረቅ አካባቢ ኖረ። ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሎጥን ሳይሆን፥ አብራምን በጣም ባረከው።
Abram and Lot Separate
Genesis 13
Abram and his nephew Lot had many animals but there was not enough food for all of them. So their shepherds started to quarrel. Abram then asked Lot to make a decision. He said, “We are relatives. It is not good to keep quarrelling! Let’s live in different areas! You choose where you want to be!” Lot chose to move to the green and fertile area beside the River Jordan. But Abram stayed in a dry region. Nevertheless, God’s blessing was with Abram, not with Lot.

የአብራም የወንድም ልጅ ሎጥ ለምለሙን መሬት ሲመርጥ
ለምለሙን መሬት ማን መረጠ?
ለምለሙን መሬት የመረጠው ሎጥ ነው።
በመጨረሻ ማን ተባረከ?
አብራም ተባረከ።
11. not ready
ዘፍጥረት 15
አንድ ቀን እግዚአብሔር አብራምን እንደገና አበረታታው። አብራም ግን ለእግዚአብሔር እስካሁን ድረስ ልጅ መውለድ እንዳልቻለ ተናገረ። አብራም እና ሦራ በጣም አርጅተው ነበር። እግዚአብሔር ለአብራም ከዋክብትን አሳይቶ “ዘርህን እንደዚህ ከዋክብት ብዙ አደርገዋለሁ” በማለት ተስፋ ሰጠው።
አብራም ልጅ ባይኖረውም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል አመነ። በአብራምም እምነት እግዚአብሔር ተደሰተ።
እግዚአብሔር በተጨማሪ የሚኖርበትን ሀገር ለወደፊት ለዘሩ እንደሚሰጥ ቃል ገባለት።
Abraham Trusts God
Genesis 15
One day God told Abram again how much he would bless him. But Abram reminded God that he still didn’t have a child. He and his wife Sarai were already very old. In response, God asked him to look at the stars in the sky and promised him, “I will make your descendants as many as the stars!”
Even though Abram didn’t have a child he believed the words that God told him. God was very pleased that Abram trusted him. And he repeated his promise that he would give the land in which Abram was living to his descendants in the future.

እግዚአብሔር ለአብራም ዘሩ እንደ ከዋክብት እንደሚበዛ ሲናገረው
አብራም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል አመነ?
አዎን፥ አብራም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል አምኗል።
12. not ready
ዘፍጥረት 16
ሦራ ለብዙ ዓመት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር። በዚህም ምክንያት በጣም ታዝን ነበር። አንድ ቀን ሦራ አጋር የተባለች የቤት ሰራተኛዋን ለአብራም ሚስት እንድትሆነው መከረችው። አብራምም እሺ በማለት አጋርን አገባት።
አጋር ልጅ ማርገዟን ስታውቅ፥ ሦራን መሳደብ ጀመረች። እግዚአብሔር ግን ለአጋር ሦራን ማሳዘን እንድትተው ተናገራት። አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት። የልጁንም ስም እስማኤል አለችው። እግዚአብሔር ለአጋር የልጇ የእስማኤል ዘሮች እንደሚበዙ ተናገራት። በልጁ ምክንያት ግን በቤተሰብ መካከል ጭቅጭቅ ሆነ።
ከጥቂት ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር ለአብራም እና ለሦራ፥ አብርሃም እና ሣራ በማለት አዲስ ስም አወጣላቸው።
Ishmael
Genesis 16
Sarai was totally discouraged because even after many years she did not have any children. And so one day she advised her husband Abram to take Hagar, her domestic servant as a wife. Abram agreed and married her.
When Hagar discovered that she was pregnant she began to offend Sarai. But God told her to stop doing that. Some time later, Hagar gave birth to a boy and named him Ishmael. God assured Hagar that Ishmael’s descendants would be many. The whole situation with the child resulted in much quarrelling within the family.
A few years later, God gave Abram and Sarai new names: Abraham and Sarah.

ልጁ ምክንያት በቤተሰብ መካከል ጭቅጭቅ ሲሆን
አጋር ሦራን ስትሰድብ እግዚአብሔር ምን አላት?
አጋር ሦራን ማሳዘን እንድትተው ተናገራት።
13. not ready
ዘፍጥረት 18፥1-15
አንድ ቀን ሦስት ሰዎች አብርሃም በሚኖርበት ሀገር በኩል ይጓዙ ነበር። አብርሃም እነማን እንደሆኑ ገና አላወቀም ነበር። ቢሆንም፥ እርሱ እና ሚስቱ ሣራ ወደ ቤታቸው አስገብተው ጥሩ ምግብ አበሏቸው። ከሰዎቹ መካከል አንዱ ለአብርሃም “በሚቀጥለው ዓመት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች” አለው። ሣራም ይህን በሰማች ጊዜ ሳቀች። ምክንያቱም በጣም ስላረጀች ልጅ ለመውለድ እንደማትችል በማሰቧ ነበር። ሰውየውም ለአብርሃም “ሣራ ለምን ሳቀች? እግዚአብሔር የማይችለው ምንም ነገር የለም” አለው።
The Visit of Three Strangers
Genesis 18:1-15
One day, three men travelled through the land where Abraham was. He didn’t know who they were. Nevertheless, he and his wife Sarah invited them into their home and served them a wonderful meal.
One of the three men said to Abraham, “In one year’s time Sarah will give birth to a son!” When Sarah heard this, she laughed, because she thought that she was already far too old to become a mother. At that, the man said to Abraham, “Why did Sarah laugh? Nothing is impossible for God!”

አብርሃም እና ሣራ ሦስቱን እንግዶች ሲጋብዙ፥ ሣራ ሰውየው የሚለውን ሰምታ ስትስቅ
አብርሃም እና ሣራ ለእንግዶቹ ምን አደረጉላቸው?
ወደ ቤታቸው አስገብተው ጥሩ ምግብ አበሏቸው።
ሣራ ለምን ሳቀች?
በጣም ስላረጀች ልጅ መውለድ የማትችል ስለመሰላት ነው።
14. not ready
ዘፍጥረት 18፥16–19፥30
ሦስቱ እንግዶች ሲሄዱ አብርሃም ሊሸኛቸው አብሯቸው ወጣ። ከሦስቱ አንዱ ግን እግዚአብሔር ነበር። እርሱም በሸለቆው ውስጥ ከሚገኙት ሀብታም ከተሞች አንዳንዶቹን ሊያጠፋ እንደሆነ ነገረው። ምክንያቱም በዚያ የሚኖሩ ሰዎች እግዚያብሔር የማይወደውን ብዙ መጥፎ ነገሮች እያደረጉ ነበር። ከእነዚህ ከተማዎች በአንዱ ሎጥ እና ቤተሰቡ ይኖሩ ነበር። አብርሃም በዚያ ቢያንስ 10 ጥሩ ሰዎች ከተገኙ፥ ከተማዎቹን እንዳያጠፋቸው እግዚአብሔርን ለመነ። እግዚአብሔርም በአብርሃም ልመና ተስማማ። ይሁን እንጂ በከተማዎቹ 10 ጥሩ ሰዎችን እንኳን አላገኘም ነበር። ስለዚህ ከተማዎቹን አጠፋቸው። ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሎጥ እና ልጆቹን ከጥፋት አዳናቸው።
Abraham Pleads for Some Evil Cities
Genesis 18:16–19:30
When the three visitors left, Abraham walked with them to see them off. He realised that one of the three men was God. And God told Abraham that he was about to destroy some of the wealthy cities down in the valley, for the people there were doing many evil things. Lot and his family lived in one of those towns. When Abraham heard about this plan, he asked God not to destroy the cities if there were at least ten good people in them. And God agreed to Abraham’s request. But he didn’t even find 10 good people there. So, he destroyed the cities, though he saved Lot and his daughters from destruction.

አብርሃም ክፉ ከተማዎችን በጥሩ ሰዎች ምክንያት እንዳያጠፋቸው እግዚአብሔርን ሲለምን
አብርሃም እግዚአብሔርን ምን ለመነው?
አብርሃም ጥሩ ሰዎች ከተገኙ፥ ከተማዎቹን እንዳያጠፋቸው ለመነው።
15. not ready
ዘፍጥረት 21
እግዚአብሔር እንደተናገረው ሣራ በዘጠና አመቷ ልጅ ወለደች። የአብርሃምም ዕድሜ መቶ ዓመት ነበር። ልጃቸውን ይስሐቅ ብለው ስም አወጡለት። የስሙ ትርጉም ሳቅ ማለት ነው። እግዚአብሔርም በይስሐቅ ምክንያት ሳቅ አደረገላቸው።
ይስሐቅ ከተወለደ በኋላ በቤተሰብ ውስጥ በእስማኤል ምክንያት ጭቅጭቁ ጨመረ። ከዚህ የተነሳ አጋር እና እስማኤል የነ አብርሃምን ቤት ለቀው ወደ ደረቅ ምድር ሄዱ። ሆኖም ግን በዚያ ቦታ እግዚአብሔር እስማኤልን ተንከባከበው።
አብርሃም ለብዙ ዓመታት ልጆች ባይኖረውም፥ እግዚአብሔር እንደተናገረው በመጨረሻ የብዙ ሕዝቦች አባት ሆነ።
Isaac
Genesis 21
Sarah finally gave birth, just as God had told her. At that time she was 90 years and Abraham 100 years old. They named their son Isaac, which means ‘laughter’. God made them laugh because of Isaac.
After Isaac was born, the quarrelling in the family increased because of Ishmael.
As a result, Hagar and Ishmael had to leave Abraham’s house and went to a dry region. God still provided for Ishmael in that place.
Even though Abraham didn’t have any children for such a long time, in the end he became the father of many nations – just like God had told him.

አብርሃም እና ሣራ ከልጃቸው ከይስሐቅ ጋር
እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋ ቃል የገባለት ልጅ ስም ማን ይባላል?
እግዚአብሔር የተስፋ ቃል የገባለት ልጅ ይስሐቅ ይባላል።
16. not ready
ዘፍጥረት 24-25
አብርሃም ከመሞቱ በፊት የቤቱን ዋና ሰራተኛ ጠርቶ ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግለት አዘዘው። ስለዚህ ሰራተኛው ወደ አብርሃም የትውልድ ሀገር ተነስቶ ሄደ። እዚያም እግዚአብሔር ሰራተኛውን ርብቃ ወደምትባል ሴት መራው። እርሷም ይስሐቅን ለማግባት እንደምትፈልግ ስትጠየቅ፥ በጋብቻው ተስማማች። ስለዚህ ከአብርሃም ሰራተኛ ጋር ወደ ይስሐቅ ሄደች።
እዚያም ከደረሰች በኋላ፥ ይስሐቅ እና ርብቃ ተጋቡ። ርብቃ ግን ልጅ መውለድ አትችልም ነበር። በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ለመነ። እግዚአብሔርም ልመናውን ሰምቶ ሚስቱ ርብቃ መንታ ልጆችን ወለደች። ስማቸውም ያዕቆብ እና ዔሳው ተባለ። ያዕቆብ የስሙ ትርጉም አታላይ ማለት ነው።
Isaac and Rebecca
Genesis 24-25
Before Abraham died, he ordered his chief servant to find a wife for Isaac. So, the servant went to Abraham’s homeland. There God led him to a young woman called Rebecca. When she was asked if she wanted to marry Isaac she agreed. And so she went with Abraham’s servant to Isaac.
Soon afterwards, Isaac and Rebecca got married. But Rebecca was not able to have children. So Isaac asked God to give them children. God heard his prayer and his wife Rebecca gave birth to twins. Their names were Jacob and Esau. The meaning of the name Jacob is ‘cheater’.

አብርሃም ሰራተኛውን ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግለት ሲያዘው
ይስሐቅን እና ርብቃን ልጅ እንዲወልዱ ማን ረዳቸው?
የረዳቸው እግዚአብሔር ነው።
17. not ready
ዘፍጥረት 25-28
ዔሳው የይስሐቅ የመጀመሪያ ልጅ ነበር። አንድ ቀን ለማደን ወደ ጫካ ሄደ። ሲመለስ በጣም ተርቦ ወደ ቤት መጣ። ወንድሙ ያዕቆብ እቤት ምስር ወጥ ሰርቶ ነበር። ዔሳውም ከሰራው ምግብ እንዲሰጠው ለመነው። ያዕቆብ ግን “የአባታችንን ርስት የማግኘት መብት ከሰጠኸኝ፥ እኔም ከሰራሁት ምስር ወጥ እሰጥሃለሁ” አለው። ዔሳውም በያዕቆብ ሀሳብ ተስማማ።
አባታቸው ይስሐቅ ከመሞቱ በፊት ዔሳውን ሊባርክ ፈለገ። በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ዔሳውን በመምሰል ወደ ይስሐቅ ሄዶ ተባረከ። በዚህ መንገድ አታልሎ የዔሳውን በረከት ወሰደበት። ዔሳው ይህንን ባወቀ ጊዜ በጣም ተናደደ። ስለዚህ ያዕቆብ ፈርቶ ከእርሱ ሸሸ። በመንገድም እያለ መሽቶ ስለነበር ተኛ። በዚያም ቦታ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦለት በእውነት እንደሚባርከው ተናገረው።
Jacob and Esau
Genesis 25-28
Esau was Isaac’s firstborn son. One day he went hunting in the forest and returned home very hungry. He saw that his brother Jacob had made lentil stew. So, he begged him to give him some of it. But Jacob said to him, “You can have some of this lentil stew, if you give me the right to the inheritance of our father.” Esau agreed to Jacob’s idea.
Before Isaac died, he wanted to bless Esau. But Jacob went to Isaac first, pretending to be Esau, and received the blessing instead of his brother. When Esau realised what had happened, he got very angry. So, Jacob became afraid and fled from him. On the journey it became dark and he went to sleep. There God appeared to him in a dream and told him that he would indeed bless him.

ዔሳው ወንድሙ ያዕቆብን ከምግቡ ሲለምን
ለምን ያዕቆብ ከሀገሩ ሸሽቶ ሄደ?
የዔሳውን በረከት በማታለል ስለወሰደበት ፈርቶት ነው።
18. not ready
ዘፍጥረት 32፥22-32
ከብዙ ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ወደ ትውልድ ሀገሩ ተመለሰ። ከቤተሰቦቹ ጋር በጉዞ ላይ እያለ አንድ ምሽት ትንሽ ራቅ ብሎ ብቻውን ሆነ። በዚያም ቦታ አንድ ሰው ወደ እርሱ መጥቶ ለረጅም ሰዓት ታገሉ።
ያዕቆብ መታገሉን ስላላቆመ፥ ሰውየው ወገቡን በኃይል መታው። በዚህ ምክንያት ያዕቆብ ማንከስ ጀመረ። ከዚህም በኋላ ሰውየው ያዕቆብን “አሁን ልቀቀኝ!” አለው። እርሱ ግን “የምለቅህ ከባረክህኝ ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት። በመጨረሻም ሰውየው “ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር ስለታገልህ፥ አዲስ ስምህን እስራኤል ብዬዋለሁ” አለው። ያዕቆብንም ባረከው።
Jacob’s New Name
Genesis 32:22-32
Many years later, Jacob returned to his homeland. While on the journey with his family, he went somewhere alone one evening. Then a man came to him and they wrestled for many hours.
Because Jacob didn’t stop wrestling, the man hit him hard on the hip. As a result, Jacob started limping. When the man said, “Let me go now,” Jacob answered, “I will only let you go if you bless me!” So the man finally told Jacob, “Because you have wrestled with people and with God, your new name will be Israel!” And he also blessed Jacob.

ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታገል
ለምን ያዕቆብ አዲስ ስም ተሰጠውu003cstrongu003e?u003c/strongu003e
አዲስ ስም የተሰጠው ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር ስለታገለ ነው።
19. not ready
ዘፍጥረት 37
ያዕቆብ አሥራ ሁለት ወንድ ልጆች ነበሩት። ከእነርሱም መካከል አንዱ ዮሴፍ ነበር። ያዕቆብ ከሌሎች ልጆቹ ይልቅ ዮሴፍን ይወደው ነበር። በዚህም ምክንያት ወንድሞቹ ጠሉት።
አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ። በሕልሙ የወንድሞቹ የስንዴ ነዶዎች ለእርሱ የስንዴ ነዶ ሲሰግዱ አየ። ያየውንም ሕልም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው “እኛ ላይ ንጉሥ የምትሆን ይመስልሃል?” ብለው ተናደዱበት። ስለዚህ ዮሴፍን ከበፊት ይልቅ ጠሉት።
Jacob’s Sons
Genesis 37
Jacob had twelve sons. One of them was called Joseph. And Jacob loved Joseph more than his other children. Because of this, his brothers hated him.
One night Joseph had a dream. In the dream he saw how his brothers’ bundles of grain bowed down before his own bundle. When he told his dream to his brothers, they were angry with him and said, “Do you think you will become our king?” Because of his dream, they hated Joseph even more than before.

ዮሴፍ ያየውን ሕልም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው
ዮሴፍ በሕልሙ ምን አየ?
ዮሴፍ በሕልሙ የወንድሞቹ የስንዴ ነዶዎች ለእርሱ የስንዴ ነዶ ሲሰግዱ አየ።
20. not ready
ዘፍጥረት 37
አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን በጎች እና ፍየሎች ሊጠብቁ ይሄዱ ነበር። አባታቸው ያዕቆብም ለዮሴፍ ምግብ ይዞላቸው እንዲሄድ ወደ እነርሱ ላከው። ወንድሞቹ ግን ገና ከሩቅ ሲያዩት ሊገድሉት ተመካከሩ። ነገር ግን ዮሴፍ እነርሱ ጋር ሲደርስ፥ በሕይወት እያለ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። በመጨረሻም ከጉድጓድ አውጥተው በዚያ ለሚያልፉ ነጋዴዎች ሸጡት። ዮሴፍ ከተሸጠ በኋላ፥ ወደ ግብጽ ሀገር ተወሰደ። እዚያም ከግብጽ መሪዎች ለአንዱ ሰራተኛ አደረጉት።
የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ቤት ከመመለሳቸው በፊት፥ አንድ ፍየል አረዱ። በደሙም የዮሴፍን ልብስ ቀቡ። ከዚያም ልብሱን ወደ ቤት ይዘው ሄዱ። አባታቸውንም በመዋሸት “የሆነ ቦታ ወድቆ አገኘነው” ብለው ሰጡት። ይህንን ባየ ጊዜ፥ ልጁ ዮሴፍ በአውሬ እንደተገደለ አመነ። ከዚህ የተነሳ ያዕቆብ በጣም አለቀሰ። ለብዙ ዓመታትም በከባድ ሐዘን ኖረ።
Joseph Sold
Genesis 37
Joseph’s brothers regularly went to herd the sheep and goats of their father. One day, their father Jacob sent Joseph to take them some food. When his brothers saw him coming from a distance, they made plans to kill him. But when Joseph arrived, they threw him alive into a deep hole. In the end, they took him out of the hole and sold him to some traders who were passing by. The traders took Joseph to the land of Egypt. There he was put to work for one of the leaders of Egypt.
Before Joseph’s brothers went home, they slaughtered a goat and stained Joseph’s robe with its blood. They took it home, gave it to their father and lied to him saying, “We found this somewhere.” When Jacob saw the robe, he cried bitterly because he believed that his son Joseph had been killed by a wild animal. He was extremely sad for many years.

ወንድሞቹ ዮሴፍን ለነጋዴዎች ሲሸጡት
ያዕቆብ እጅግ አዝኖ የነበረው ለምንድን ነውu003cstrongu003e?u003c/strongu003e
ያዕቆብ ያዘነው ልጁ ዮሴፍ በአውሬ የተገደለ ስለመሰለው ነው።
በእርግጥ ዮሴፍ ሞቶ ነበርu003cstrongu003e?u003c/strongu003e
ዮሴፍ ወንድሞቹ ሸጠውት እንጂ አልሞተም ነበር።
21. not ready
ዘፍጥረት 39
ዮሴፍ የግብጽ ሀገር የጦር አለቃ ቤት አስተዳዳሪ ሆነ። ቆንጆም ወጣት ስለነበር፥ የአለቃው ሚስት ከእርሱ ጋር ያልተፈቀደ ነገር ማድረግ ፈለገች። ዮሴፍ ግን “እኔ ባልሽ አይደለሁም። በጌታዬ ላይ ይህንን መጥፎ ነገር ማድረግ አልፈልግም። ይህ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት የተከለከለ ነው” ብሎ መለሰላት።
ሴትዮዋ ግን ደጋግማ ጠየቀችው። በመጨረሻም ዮሴፍ የለበሰውን ልብስ ያዘች። ዮሴፍ ግን ልብሱን ጥሎላት ሸሸ። እርሷም በጣም ተናደደችበት። የቤቷን ጠባቂዎች ጠርታ “መጥፎ ነገር ሊያደርግብኝ ፈልጎ ነበር። ስጮህ ግን፥ ልብሱን ጥሎ ሄደ” ብላ በውሸት ከሰሰችው። ባሏም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ዮሴፍን ወደ እስር ቤት አስገባው።
The Wife of Joseph’s Master
Genesis 39
In Egypt, Joseph became the manager of the army commander’s house. Because he was a handsome young man, his master’s wife wanted to do something forbidden with him. But Joseph told her, “I am not your husband! I don’t want to do that to my master! And it would also be wrong before God!”
But the lady didn’t stop nagging him. Finally, she grabbed him by his clothes, but Joseph threw them off and ran away. Now the lady became very angry indeed. She called the guards of the house and accused Joseph falsely with the words, “He wanted to do something bad to me. But when I shouted, he left his clothes and ran away.” When her husband heard about all this, he put Joseph in prison.

ሴቲቱ ዮሴፍን በያዘችው ጊዜ ልብሱን ትቶ ሲሸሽ
ዮሴፍ ለምን ሴትዮዋ የጠየቀችውን ጥያቄ እንቢ አለ?
የጠየቀችው በእግዚአብሔር ፊት የተከለከለ ነገር ስለሆነ ነው።
22. not ready
ዘፍጥረት 41
አንድ ሌሊት የግብጽ ንጉሥ ሕልም አየ። ነገር ግን የሕልሙን ትርጉም ሊነግረው የሚችል ማንም ሰው አልተገኘም። በመጨረሻ ንጉሡ ዮሴፍ ሕልም የመተርጎም ስጦታ እንዳለው ሰማ። ስለዚህ ዮሴፍን ከእስር ቤት አስጠርቶ ሕልሙን እንዲተርጉምለት ጠየቀው። ዮሴፍም ንጉሡን “የሕልምን ትርጉም ሊያሳውቅ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው” አለው።
ከዚያም ንጉሡ ያየውን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ ነገረው፡ “በመጀመሪያ ሰባት ወፍራም ላሞችን፥ ቀጥሎም ሰባት ቀጫጭን ላሞች አየሁ። ከዚያም በኋላ ቀጭኖቹ ላሞች ወፍራሞቹን ላሞች ሲበሉ አየሁ” አለው። ዮሴፍም እንዲህ ሲል ሕልሙን ተርጎመለት “እግዚአብሔር ይህንን እንድታውቅ ይፈልጋል:- በመጀመሪያ መልካም የእህል ምርት የሚገኝበት ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። ከዚያ በኋላ ግን ሰባት አስቸጋሪ የራብ ዓመታት ይመጣሉ። በዚያን ጊዜ የመልካም ዓመታት ሀብት ሁሉ በፍጥነት ይጠፋል። ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በመልካሙ ጊዜ አስቀድመህ መዘጋጀት ይኖርብሃል” አለው።
The Dream of Egypt’s King
Genesis 41
One night the King of Egypt had a dream. But no one was able to tell him its meaning. Finally, the king heard that Joseph had a gift to interpret dreams. So he had him come from prison and asked him to tell him the meaning of his dream. At this, Joseph responded, “Only God can reveal the meaning of dreams!”
Then the king told Joseph his dream, “First I saw seven fat cows and later I saw seven thin cows. Then I saw the thin cows eat up the fat cows.”
Joseph explained the dream to him, “God wants you to know this: First there will be seven good years of harvest. After that there will be seven difficult years of hunger. At that time all the wealth of the good years will quickly disappear. Therefore, make thorough preparations during the good time, oh king!”

የግብጽ ንጉሥ ሰባት ወፍራም ላሞች እና ሰባት ቀጫጭን ላሞች በሕልሙ ሲያይ
ትክክለኛውን የሕልም ትርጉም ሊያሳውቅ የሚችል ማን ነው?
ትክክለኛውን የሕልም ትርጉም ሊያሳውቅ የሚችለው እግዚአብሔር ነው።
23. not ready
ዘፍጥረት 41-42
ነጉሡ ዮሴፍ ሕልሙን ከተረጉመለት በኋላ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፥ በእህል ምርት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ባለ ሥልጣን አድርጌሃለሁ” አለው። ዮሴፍን በሥልጣን የሚበልጠው ንጉሡ ብቻ ነበር። ስለዚህ ዮሴፍ በሰባቱ መልካም ዓመታት የእህል ምርት እንዲሰበሰብ አዘዘ። በመንግሥትም የእህል ማስቀመጫ በሆኑት ጎተራዎች እንዲቀመጥ አስደረገ።
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ እንደተናገረው ሰባት የራብ ዓመታት መጡ። በዚያን ጊዜ ከተቀመጠው እህል ሸጦ የግብጽን ሕዝብ ከሞት አዳናቸው።
በረሃቡም ምክንያት ደግሞ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ሊገዙ ከከነዓን ሀገር መጡ። ዮሴፍ ባያቸው ጊዜ ወዲያውኑ አወቃቸው። እነርሱ ግን አላወቁትም ነበር። ዮሴፍ በፍፁም ደግነት እህል ሰጣቸው። ሆኖም ግን ወንድማቸው እንደሆነ ገና አልነገራቸውም። እህሉን ከተቀበሉ በኋላ፥ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ።
Joseph Becomes a High Leader
Genesis 41-42
After Joseph interpreted the dream, the king said, “I am putting you in charge of all grain supplies, because God is with you.” This meant that only the king had more power than Joseph. Therefore, Joseph commanded to collect and put huge amounts of grain into the storages of the government during the seven good years.
Then, just as Joseph had told, the seven years of famine came. At that time, he sold the grain, and in this way, saved the people of Egypt from starving to death.
Due to the famine, Joseph’s brothers came from Canaan to buy grain. When Joseph saw them, he recognised them immediately. However, they didn’t recognise him. Joseph kindly gave them grain. But he didn’t tell them who he was. After his brothers received grain they went back to their country.

ዮሴፍ እህል ለወንድሞቹ ሲሰጥ
ዮሴፍ ብዙ ክፉ ነገር ላደረጉበት ወንድሞቹ ምን አደረገ?
ዮሴፍ በፍፁም ደግነት እህል ሰጣቸው።
24. not ready
ዘፍጥረት 43-46
የዮሴፍ ወንድሞች እንደገና እህል ለመግዛት ወደ ግብጽ መጡ። በዚህ ጊዜ ዮሴፍ “እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። እግዚአብሔር ሁላችሁንም ከዚህ ራብ ለማትረፍ ፈልጎ እኔን ወደዚህ እንድመጣ አደረገ” አላቸው። ወንድሞቹ ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ። ዮሴፍ ግን የሰሩበትን ክፉ ስራ ሁሉ ይቅር ስላላቸው፥ አልተቆጣቸውም። እንዲያውም እንደገና ስላያቸው በጣም ተደስቶ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
ከዚያም ዮሴፍ ያዕቆብ እና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ መጥተው እንዲኖሩ ጋበዛቸው። እነርሱም ተስማምተው ወደ ግብጽ መጡ። እዚያም በደረሱ ጊዜ ያዕቆብ ልጁ ዮሴፍን በሕይወት ስላገኘው እጅግ ደስ አለው።
Jacob and His Family Move to Egypt
Genesis 43-46
Later, Joseph’s brothers came to Egypt again to buy grain. This time Joseph told them who he was. He said, “I am your brother Joseph. God brought me here, because he wanted to save you all from this famine.” When his brothers heard this, they were extremely afraid. But Joseph was not angry with them, because he had forgiven them all their evil deeds. In fact, he was very happy to see them again. So he wept loudly for joy.
Then Joseph invited his whole family to come and live in Egypt. Back at home, Jacob and his family decided to accept the invitation. And so they moved to Egypt. When they arrived there, Jacob was overjoyed to find Joseph, his son, alive.

ዮሴፍ ወንድሞቹን በማየቱ እጅግ ደስ አለው። ወንድሞቹ ግን ፈሩት።
ለምን ዮሴፍ በወንድሞቹ አልተናደደም?
ዮሴፍ እግዚአብሔር ሰዎችን ከራብ ለማዳን እንደላከው ስለተረዳ እና የሰሩበትን ክፉ ስራ ሁሉ ይቅር ስላላቸው ነው።
25. not ready
ዘፍጥረት 48-49
ያዕቆብ በግብጽ ሀገር ሲኖር ሳለ በጣም አረጀ። ከመሞቱ በፊት የዮሴፍን ልጆች ትልቅ በረከት ባረካቸው። ከታላቅ ልጁ ይልቅ ኤፍሬም ለተባለ ታናሽ ልጁ የበለጠ በረከት ሰጠው። ይህንን ለማሳየት ያዕቆብ ሲባርካቸው ቀኝ እጁን አሻግሮ በኤፍሬም ላይ፥ ግራ እጁን ደግሞ በወንድሙ ላይ አደረገ። ሆኖም ግን ሁለቱንም በደንብ ባረካቸው።
ከዚያ በኋላም የራሱን አሥራ ሁለት ወንድ ልጆቹን ጠርቶ እያንዳንዳቸውን ለየብቻቸው ባረካቸው። ወደፊት በእነርሱ ስለሚሆነውም ነገር ነገራቸው።
የያዕቆብ ዘሮች በጊዜ ሂደት አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ።
Jacob Blesses His Sons and Grandsons
Genesis 48-49
Jacob grew very old in Egypt. Before he died, he gave his greatest blessing to Joseph’s sons, especially to Ephraim who was the youngest. To show this, Jacob crossed his arms when he said the blessing. So he put his right hand on Ephraim and his left hand on his brother. In any case, Jacob blessed both of them thoroughly.
Later, he summoned his own 12 sons and blessed each one of them individually. He also talked to them about what would happen to them in the future.
Over time, the descendants of Jacob became the 12 tribes of Israel.

ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች እና የራሱን ልጆች ሲባረካቸው
ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት ምን አደረገ?
ልጆቹን እና የልጅ ልጆቹን ባረከ።


በታሪክ 1-25 ፈልግ፡